የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሠራተኞች የተረከቡትን የወ/ሮ ጃለሌ ወርቁ የመኖሪያ ቤት ግንባታ ጀምረዋል።

    በበሀገር አቀፍ ደረጃ በየአመቱ በሚከናወነው የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ጰጉሜ 1 ቀን የበጎነት ቀን ሆኖ በመሰየሙ በዛሬው እለት የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ በቀበሌ 04 ከ83 ዓመተ ምህረት ጀምሮ በክራይ ቤት ሲኖሩ ለነበሩት ለአንድ አቅመ ደካማን ቤት ለመገንባት ስራ ጀምረዋል።
    እንደ አስተዳደር የሚያስተባብር ኮሚቴ በአስተዳደር ደረጃ በዚህ ክረምት ለአቅመ ደካሞች ለሚገነቡ ከተመረጡ ቤቶች መካከል አንዱ በ04 ቀበሌ በተሰጣቸው ቦታ ለወ/ሮ ጃለሌ ወርቁ ቤት መገንባት ለተቋሙ በመሰጠቱ ግንባታውን ለማስጀመር የቤቱ የንድፍ ስራውን ጨምሮ ሌሎች የቅድመ ዝግጅት ስራዋች መጠናቀቃቸውን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ብሩክ ፈለቀ በመግለፅ ይህን መሰል በጎ ስራ በየአመቱ በተቋማቸው እንደሚከናወን ገልፀዋል።
    በዛሬው እለትም የቤቱ ግንባታ የተጀመረ ሲሆን በመረሀ ግብሩም ማስጀመሪያ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ብሩክ ፈለቀ ፣የኢመንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሙአዝ አሊ፣የመረጃ ማፍራትና ማብቃት ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ወንደሰን አባይ ፣ የለውጥና መልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር መስከረም ተ/ሀይማኖት እና የቢሮው ሠራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል።
    በጎነት ለራስ ነው!!!!
    በትዕግስት ቶሎሳ
    ፎቶ፦በዮናስ ደበበ