በድሬዳዋ አስተዳደር ለሚገኙ ወጣቶች በቀውስ ጊዜ ኮሚዩኒኬሽን ስትራቴጂ ዙሪያ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ ።

    በድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አዘጋጅነት በዛሬው እለት በድሬዳዋ አስተዳደር በዘጠኙም የከተማ ቀበሌዎች ላይ ለሚኖሩ ወጣቶች የቀውስ ጊዜ ኮሚዩኒኬሽን ስትራቴጂ ዙሪያ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጥቷል ።
    በዚሁም መርሀ-ግብር ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ምክትል ሀላፊና የፖለቲካና ርእዮተ አለም ዘርፍ ሀላፊ የሆኑት አቶ ሻኪር አህመድ አሁን ላይ ሀገራችን ኢትዮጲያ የቀውስ ጊዜ ኮሚዩኒኬሽን በእጅጉ እንደሚያስፈልጋትና ወጣቶችም በሚዲያዎች ላይ የተሻሉ ስራዎችን በመስራት ሀገራችንን ማሳደግ እንደሚገባቸው ተናግረው በቀጣይም እንደዚህ አይነት መሰል የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ነው አቶ ሻኪር በእለቱ ያስታወቁት ።
    በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የሚሰሩ ስራዎች ለሀገር ከፍተኛ ጠቀሜታ ስላላቸው በአቅም ግንባታ ስልጠናው ላይ ተሳታፊ የሆኑ ወጣቶች በስልጠናው ላይ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ በቀጣይ የተሻሉ ስራዎችን ለመስራት መትጋት እንደሚገባቸው የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሀላፊ የሆኑት አቶ ብሩክ ፈለቀ ተናግረዋል ።
    በአለማየሁ አበበ ።
    ፎቶ :- በይድነቃቸው አብርሃም ።