የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የ2014 የስራ አፈጻጸም ሪፖርትና የ2015 ዓ.ም ዕቅድ ለኮሌጁ ቦርድ ቀርቦ ተገመገመ።

    በዚህም የኮሌጁ ቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት የንግድ፣ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ የተሰሩትን ስራዎች አድንቀው በቀጣይ በተለይም አዳዲስ ሰልጣኞችን ለመቀበል የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እንዲሁም ከኢንዱስትሪዎች ጋር የሚኖረውን ትስስር ማሻሻል ላይ ትኩረት ሊደረግ ይገባል ብለዋል።
    አያይዘውም በካይዘን ትግበራ ጥሩ አፈጻጸም እያሳዩ የሚገኙ የዉድ ቴክኖሎጂ እና ኤሌክትሪካል ኤሌክትሮኒክስ ዲፓርትመንቶችን በመዘዋወር የጎበኙ ሲሆን የዚህ ለውጥ ባለቤት የሆኑትን አሰልጣኝ መምህራንንም አበረታተዋል።
    የስራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት