ፖሊስ የዜጎችን ሰላምና ደህንነት ከማረጋገጥ በተጨማሪ የህብረተሰቡን ማንኛውንም ችግር ለመፍታት የሚተጋ መሆኑ ተገለጸ

    የለገሀሬ ፖሊስ ጣቢያ ለችግር ለተጋለጡና ድጋፍ ለሚሹ አንድ መቶ ተማሪዎች የትምህርት መርጃ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ
    የለገሀሬ ፖሊስ ጣቢያ የአካባቢውን ባለሀብቶችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን በማስተባበር አንድም ተማሪ ከትምህርት ገበታ ሊቀር አይገባም በሚል ከሰባ ሺ ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው የትምህርት መርጃ ቁሳቁሶችን ለችግር ለተጋለጡና ድጋፍ ለሚሹ ተማሪዎች በድጋፍ አብርክቷል::
    በድጋፍ መድረኩ የተገኙት በድሬዳዋ ፖሊስ የሰው ሀብት ልማት አስተዳደር ዳይሬክቴር ረ/ኮሚሽነር ጌታሁን አበራ የለገሀሬ ፖሊስ ጣቢያ በመደበኛ ተቋማዊ ተልዕኮ የተለያዩ የለውጥ ስራዎችን በውጤታማነት እያከናወነ እንደሆነ ተናግረው በዛሬ እለትም የተቸገሩ ወገኖችን በማሰብ ጣቢያው ያደረገው የመማሪያ ቁሳቁሶች ድጋፍ እጅጉን የሚያስመሰግን ነው ካሉ በሃላ ድጋፍ ላደረጉ አካልት በሙሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል::
    የለገሀሬ ፖሊስ ጣቢያ ዋና አዛዥ ኢ/ር መሀመድ አህመድ በበኩላቸው ጣቢው ከፖሊሳዊ አገልግሎት ባለፈ በሰብአዊነት የማገልገል መርህን በመከተል የተለያዩ የበጎ ፍቃድ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ተናግረው በቀጣይም ይህን መሰል የተቸገሩና ድጋፍ የሚሹ ወገኖችን የመደገፍ ስራዎች ቀጣይነት ባለው መልኩ የሚሰራ ይሆናል ብለዋል::
    በመድረኩ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የጥናትና ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ሳፊያ ዩሱፍ ቢሮውን ወክሎ በመገኘት ለተደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን ያቀረቡ ስሆን በተመሳሳይ የቢሮው የህፃናት ልማትና ደህንነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሪተ ነዒማ ኢብራሂምም በበኩላቸው ፖሊስ ከዚ በፊትም የህፃናቱን ደህንነት ከማስጠበቅ አንፃር ከቢሮው ጋር በመቀናጀት ሰፊ ስራ እየሰሩ በመሆናቸው በተጨማሪም ለችግር ተጋላጭ የሆኑ ህፃናት ከደሞዛቸው በመቁረጥ እየደገፉ እንደሚገኙ በመግለጽ ለዛሬም ሆነ ለሁልጊዜ ድጋፋቸው በህፃናቱና በቢሮው ስም ለፖሊስ አባላቱ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
    የድጋፍ መርሀ ግብሩም የአስተዳደሩ የቀበሌ 08 ጽህፈት ቤት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አብዱልአዚዝ አሜን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ፣ የሀይማኖት አባቶችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍል ተወካዮች በተገኙበት የተካሄደው ስሆን ይህንኑ በጎ ተግባር በተለያዩ መንገዶች ለደገፉና ለአስተባበሩ አካልትም ምስጋናና እውቅናም በመድረኩ ተሰጥቷል።
    ምንጭ:- – ድሬ ፖሊስ የህዝብ ግንኙነት
    – የድሬዳዋ አስተዳደር ሴቶች
    ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ