የኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ በሽታን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በተሰሩት ስራዎች የድሬዳዋ ሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሚና ከፍተኛ እንደነበር ተገለፀ ።

    የኢትዮጲያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከኢ.ፌ.ድ.ሪ ጤና ሚኒስቴር ጋር በጋራ በመተባበር ከኮሮና ቫይረሰ ወረርሺኝ በሽታ ጋር ተያይዞ ወቅታዊ መረጃዎችንና የተግባቦት መንገዶችን በመጠቀም ረገድ የአባል ሃይማኖት ተቋማትን አቅም ማጎልበቻ እንዲሁም ተላላፊ የሆኑና ያልሆኑ በሽታዎችን ለመከላከል ብሎም ወቅታዊ መረጃን ለመስጠት ይቻል ዘንድ በዛሬው እለት በ ቢ ካፒታል ሆቴል መሰብሰቢያ አዳራሽ የግንዛቤ ማስጨበጫ ተሰጥቷል ።
    በዚሁም መድረክ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ሀላፊ የሆኑት ወ\ሮ ለምለም በዛብህ የጤና ስራ በጤና ተቋማት ወይም ባለሞያዎች በሚሰሩት ስራዎች ብቻ ውጤታማ መሆን እንደማይቻልና ላለፍት አመታትም በተፈጥሮም ሆነ በሰው ሰራሽ ምክንያት የሚከሰቱ የጤና ችግሮች ላይ በጋራ በመሆን ሲሰራ መቆየቱን ወ\ሮ ለምለም በዛብህ ተናግረው የድሬዳዋ ሀይማኖት ተቋማት ጉባኤም የኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ በሽታ በተከሰተበት ወቅት ብሎም በሌሎችም የጤና ጉዳዮች ላይ ከጤና ቢሮ ጋር በጋራ በመሆን በመስራት ለውጥ ማምጣት መቻሉንም ነው ሀላፊዋ የተናገሩት ።
    የጤና ሚኒስቴር አለም አቀፍ ወረርሺኝ የሆነው የኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ በሽታ በአለም አቀፍ ደረጃ ስጋት ከሆነበት እለት አንስቶም ሆነ በሀገራችን ኢትዮጲያ ላይም ከተከሰበት እለት አንስቶ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ወረርሺኙን ለመከላከልና ለመቆጣጠር እንዲሁም ወረርሺኙ የሚያስከትለውን ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጫና ለመቀነስ በርካታ ስራዎች ሲሰራ መቆየቱን በኢ.ፌ.ድ.ሪ ጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ከፍተኛ አማካሪ የሆኑት ዶክተር ሙሉቀን ዩሀንስ በእለቱ ተናግረዋል ።
    በግንዛቤ መስጨበጫ መድረኩ ላይም የሀረሪ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስትና የሱማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ምክትል ሀላፊዎች እንዲሁም የሀይማኖት አባቶች ተሳታፊ ሆነዋል ።
    በአለማየሁ አበበ ።
    ፎቶ :- ሰላም አበበ ።