በገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ የተመራ የልዑካን ቡድን የድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠናን ጎብኝቷል፡፡
የድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠናን ለማሳደግ፣ አገልግሎቱን ለማስፋፋት እና የታለመለትን ግብ ለማሳካት መንግስት ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አቶ አህመድ ሽዴ አረጋግጠዋል።
ነፃ የንግድ ቀጠናውን ለማሳደግ እና ለማሻሻል ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት እንዲሰሩ ጥሪ ማቅረባቸውን ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በጉብኝቱ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሳንዶካን ደበበ እና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጀዋርን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡
የድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠናን ለማሳደግ አስፈላጊው ድጋፍ ይደረጋል – አቶ አህመድ ሽዴ የድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠናን ለማሳደግ፣ አገልግሎቱን ለማስፋፋት እና የታለመለት ግብ እንዲሳካ አስፈላጊው ድጋፍ ይደረጋል ሲሉ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ተናገሩ፡፡


