የድሬዳዋ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ የትምህርት ቁሳቁሶችን የማሟላት አቅም ለሌላቸው የአስተዳዳሩ ተማሪዎች የሚውል የደብተር እና ስክሪብቶ ድጋፍ አደረገ።

የድሬዳዋ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ በአስተዳደሩ የሚገኙ የመንግስት ተቋማትን አገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል እየሰራ ከሚገኘው ዘርፈ ብዙ ተግባራት ጎንለጎን እንደ ተቋም ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣትም የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ ነፈይገኛል።

ቢሮው እየተወጣቸው ማህበራዊ ኃላፊነቶች መካከል አነዱ በቅርቡ በ01 ቀበሌ የተረከበው እና ግንባታውን በማጠናቀቅ ላይ ነፈየሚገኘው የወ/ሮ አሁዶ የመኖሪያ ቤት አንዱ ሲሆን በዛሬው እለት ደግሞ በአስተዳደር ደረጃ አንድም የነገ ሀገር ተረካቢ የሆነ ተማሪ የትምህርት ቁሳቁስ በማጣት ትምህርቱ እንዳይስተጓጎል እየተደረገ ያለውን ጥረት ለመደገፍ 50 ደርዘን የደብተረ እና 5 ፓኬት የስክሪብቶ በአጠቃላይ 46,000(አርባ ስድስት ሺህ) ብር ግምት ያለው የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ በቢሮው ኃላፊ አቶ ሀይር ሀጂኑር አማካኝነት የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ሰቦ አህመድ እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ለድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አስረክቧል ።
© ፐብሊክ ሰርቪስና ሰዉ ሀብት ልማት ቢሮ ኮሙኒኬሽን