የድሬዳዋ የቀድሞ ከንቲባ ክቡር አልፍሬድ ሻፊ ቤተሰቦች ለአስተዳደሩ ምስጋናቸውን አቀረቡ።
ቤተሰቡ ከምስጋናው በተጨማሪም ለድሬዳዋ ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር የግማሽ ሚሊየን ብር የገንዘብ ስጦታ በግል አበርክቷል። በድሬዳዋ ዘመናዊ የከተማነት ስልጣኔ ታሪክ ውስጥ፤ ጉልህ ሚና ከነበራቸው ተጠቃሽ አመራሮች መካከል፤ የቀድሞው ክቡር ከንቲባ አልፍሬድ ሻፊ ዋነኛው ናቸው። ከንቲባው በመሪነት ዘመናቸው ለድሬዳዋ ያበረከቱት የልማት ትሩፋትና ህዝብን የማስተዳደር መልካም ስማቸው ለትውልድ በክብር እንዲተላለፍ፤ እርሳቸው ያስገነቡት ጥንታዊው የኮኔል ድልድይ “የአልፍሬድ ሻፊ…


