የድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት የበጀት ኢኮኖሚ ንግድና ኢንደስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለ4ኛ ቀን የመስክ ምልከታውን ቀጥሎ ያካሄደ ሲሆን በዛሬው እለት የድሬደዋ አስተዳደር ባህል እና ቱሪዝም ፅ/ቤት እና በቱሪዝም ሚኒስቴር ቅንጅት እየተሰራ ያለ ላንድ ማርክ ፕሮጀክት አፈፃፀም ያለበትን ደረጃ ምልከታ ካደረገ በኋላ ከዚራ የሚገኘውን የቅዱስ ሚናስ ቤተ ፀሎት፣ የአርመን ሀዋሪያዊት ቤተክርስቲያን እና ለገሀሬ ገንደ- ገበሬ የሚገኘውን የህንዶች ባሊያን አስክሬን ማቃጠያ ግቢ ያሉ ታሪካዊ ቅርሶችን እንዲሁም ዋሂል ክላስተር ሀርላ ቀ/ገ/ማህበር በመገኘት ለ ኦፕን ሙዚየም የሚያገለግሉ ከመሬት ውስጥ የተገኙ ቤቶች እና ሀርላ የማህበረሰብ ሙዚየም ውስጥ የሚገኙ ታሪካዊ ቅርሶች ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን ድሬዳዋ ለማስተዋወቅ እና ለቱሪዝም እንደስትሪው ዘርፍ ለማሳደግ ባህላዊ እና ታሪካዊ ቅርሶችን በተመለከተ ያሉ ችግሮችን በአግባቡ በመለየት ለቅርሶችን አሰፈላጊ ጥበቃ እና እንክብካቤ ለማድረግ ፅ/ቤቱ ከሌሎች ተቋማት እና ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መስራት እንዳለበት ቋሚ ኮሚቴው አሳስቧል።
በመቀጠልም ቋሚ ኮሚቴው የድሬ ብድርና ቁጠባ ተቋም የተዘዋዋሪ ፈንድ ብድር እና ሌሎች የብድር አወሳሰድና አመላለስ ዙሪያ ያለው አፈፃፀም እንዲሁም ከተቋማት ጋር ያለውን ቅንጅታዊ አሰራር መገምገማቸውን የበጀት ኢኮኖሚ ንግድና ኢንደስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ አይናለም ተዘራ ገልፀዋል ።


