ባለፉት 3 ቀናት ሲካሄድ የቆየው የብልፅግና ፓርቲ የ6ወራት የስራ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ ተጠናቋል
በማጠቃለያ መርሀ ግብሩ ላይ በፓርቲያችን ምክትል ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ አደም ፋራህ ለቀጣይ ስራ አቅጣጫዎች ስኬታማነት አቅም መፍጠር የሚችሉ የስራ መመሪያዎች ተሰጥተዋል።
በሪፖርቶች የተመላክቱ የአፈፃፀም ችግሮች እንዲታረሙ፣በጥንካሬ የተነሱ ነጥቦች ይበልጥ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ፣ በተለያዩ ክልሎች ያሉ እምቅ ሀብቶች በተደራጀ አቅም መውጣት እንዲችሉ፣ አመራሩ ምልአተ ህዝቡን በማሳተፍ መንቀሳቀስ እንደሚገባው በመድረኩ የቆይታ ቀናት በሚገባ ተመላክቷል።
“ከዕዳ ወደ ምንዳ” በሚል መሪ ሀሳብ ለ4 ተከታታይ ዙሮች የተሰጠው ሀገር አቀፍ የስልጠና መርሀ ግብር የተሳካ እንዲሆን አስተዋፆ ላበረከቱ አካላት የእውቅና መርሀ ግብር ተካሄዶል።
በዚህም የእውቅና እና የምስገና መረሀ ግብር የድሬዳዋ ብልፅግና ፖርቲ ጽ/ቤት ሽልማት ተበርክቶለታል።
በመርሀ ግብሩ ላይ የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ አደም ፋራህን ጨምሮ የፓርቲያችን ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
የመረጃ ምንጭ፦ የኢትዮጰያ ብልፅግና ፖርቲ


