የኢ.ፌ.ድ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ(ዶ/ር) የሁለተኛው ትውልድ ኢትዮጲያውያን ዲያስፖራዎች ወደ ሀገር ቤት እንዲገቡ ያስተላለፍትን ጥሪ ተከትሎ ወደ ከተማችን ድሬዳዋ በርካታ ዲያስፖራዎች የመጡ ሲሆን የድሬዳዋ አስተዳደር ለእንግዶች የተለያዩ መርሀ ግብሮችን በማዘጋጀት ድሬዳዋዊ መስተንግዶ እያደረገ ይገኛል።
በዛሬው ዕለት ዲያስፖራዎቹ በከተማዋ ያሉ ግዙፍ የልማት ስራዎች የጎበኙ ሲሆን ማምሻውን ደግሞ በክብር ዶ/ር አሊ ቢራ ፖርክ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የንግድ ኢንድስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ የተከበሩ ሀርቢ ቡህ በተገኙበት የእራት ግብዣ እየተከናወነ ይገኛል።
በመርሀ ግብሩ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ክብርት ፈቲያ አደንና የካቢኔ አባላት እንዲሁም በአስተዳደሩ ከፍተኛና እንዲሁም በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ተገኝተዋል።


