የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ እና የምክር ቤቱ አባላት ታላቁ የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየምን ጎበኙ

የኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ እና የምክር ቤቱ አባላት ታላቁ የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየምን ጎብኝተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፤ የኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤንና የምክር ቤቱን አባላት ታላቁ የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየምን ማስጎብኘታቸውን ማህEBCበራራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።

የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የኢትዮጵያውያን የአብሮነት፣ የአንድነትና የአሸናፊነት ተምሳሌት የሆነው የዓድዋ ድል የታሪክ ስብራት የሚጠግን እና ለትውልድ የሚተላለፍ ሕያው ታሪክ ሆኖ መገንባቱን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላቱ በጉብኝት ወቅት ገልፀውልናል ሲሉም ከንቲባዋ አክለዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *