የአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የጋራ ታሪካችንን በመዘከር አንድነታችንን የምናጠናክርበት እና የወደፊት ብልጽግናችንን የምናረጋግጥበት ነው ሲሉ የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ ገለጹ።
የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ ታገሰ ጫፎ እና የምክር ቤቱ አባላት የአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየምን ጎብኝተዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ኘሮጀክትን በተመለከተ ለጎብኝዎቹ ገለፃ ያደረጉ ሲሆን፤ በኘሮጀክቱ በመሳተፉ አሻራቸውን ላስቀመጡ ሁሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
በጉብኝቱ የምክር ቤቱን አፈ- ጉባዔ አቶ ታገሰ ጫፎን ጨምሮ ምክትል አፈ ጉባዔ፣ የመንግስት ተጠሪ እና ሌሎች የምክር ቤቱ አመራሮች እና አባላት መሳተፋቸውን ምክርቤቱ መረጃ ያመላክታል፡፡
EBC


