በመድረኩ ባለፉት ስድስት ወራት በሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት በጋራ የሚገመገምበት ነው።
በግምገማ መድረኩም የድሬዳዋ አስተዳደር መንግስት ኮሙዩኒኬሽን እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደሮች የ6 ወር ሪፖርታቸውን አቅርበዋል።
በመድረኩ የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የ6 ወር ሪፖርት በተቋሙ ኃላፊ በአቶ ብሩክ ፈለቀ አማካኝነት ቀርቧል።
የመድረኩ ተሳታፊዋች በድሬዳዋ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን በቀረቡ ሪፖርት በሚዲያ ዳሰሳ እና በህዝብ አስተያየት እንዲሁም የሀይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዋች ጋር አብሮ በመስራት የአብሮነት እና የመቻቻል እሴታቸውን የሚገነቡበት ተሞክሮ እና ቢሮው በመንግስትና በህዝብ መሀል እየፈጠረ ያለው የተግባቦት ስራ ለየት ያለ በመሆኑ ሌሎች ክልሎችም ይህን ተሞክሮ ልንጋራው ይገባል ብለዋል ።
የድሬዳዋ ኮሙዩኒኬሽን ተቋሙ ለሚዲያው የመረጃ ግብአትነት ክፍት በመሆናቸው በሌሎች አካባቢዋች የሚኖሩ ነዋሪዋች ድሬዳዋ እንዲያውቋት ከማስቻሉም በላይ መረጃዋችን በተራጀ መልኩ ለህዝብ ተደራሽ ማድረግ ተችሏል ብለዋል።
የድሬዳዋ አስተዳደር መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ


