ዓለም ዓቀፉ የመኪና አምራች ሚትስቡሺ በድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና በትሬዲንግ የሚገኙ የኢንቨስትመንት አማራጮችን ለመጠቀም ፍላጎት እንዳለው መግለጹን የኢንዱስትሪ ፖርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አስታወቀ።
የኩባንያው ስራ አስኪያጅ ሺግዮሺን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከሚያስተዳድራቸው የኢንቨስትመንት ማዕከሎች መካከል ሐዋሳ፤ አዳማ እና ቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን ጎብኝተዋል።
የኮርፖሬሽኑ የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽንና ማርኬቲንግ ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዘመን ጁነዲን ኩባንያውን ስራ አስኪያጅ ሺግዮሺን ጋር ተወያይተዋል።
በስራ አስኪያጁ ድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠናም ከትሬዲንግ ጋር የተያያዙ ኢንቨስትመንቶች ላይ መሰማራት እንደሚፈልግ ገልፀው፤ኩባንያው ለኢንቨስትመንቱ የሚረዱ ቅድመ ጥናቶችን ማከናወን እንደሚፈልግ ማስረዳተቻውን ከኮርፖሬሽኑ ያገነነው መረጃ ያመለክታል።
አቶ ዘመን በበኩላቸው፤ ድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና አሁን ላይ በኢንቨስትመንት ትልቅ ፍላጎትና የተለያዩ ዘርፎችን እያስተናገደ የሚገኝ የድሬዳዋ አዲስ መልክ መሆኑን ጠቁመው፤ ሚትስቡሺ ለትሬዲንግ ኢንቨስትመንት የሚረዳውን ጥናት እንዲያደርግና በዘርፉ እንዲሰማራ ኮርፖሬሽኑ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።
ሚትስቡሺ ኩባንያ ተቀማጭነቱን በጃፓን ቶኪዮ ያደረገ፤ በተሽከርካሪ ምርት የሚታወቅና በባንኪንግ፤ በአግሮ ፕሮሰሲንግ፤ በኬሚካል ኢንዱስትሪ እና በሌሎችም ግዙፍ ኢንቨስትመንቶች የተሰማራና ዓለም አቀፍ ተቋም ነው።
E BC


