#ዜና ዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመጠቀም የፉይናስ ስርአቱን ለማዘመን እየሰራ እንደሚገኝ የድሬዳዋ አስተዳደር የገንዘብ ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ አስታወቀ

የገንዘብ ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የኘላንና ኢኮኖሚ ልማት ኮሚሽን የፉይናስ፣የድጋፍ እና የክትትል ስርአቱን ለማዘመን የኘሮጀክቶች የድጋፍና ክትትል እና አንድ እቅድ አንድ ሪፖርት በአቶሜሽን ሶፍትዌር ወደ ስራ መግባቱን ይታወሳል በዛሬው እለትም በሦስተኛነት

የበጀት አገልግሎት አሰጣጥ የሚያሳድግ (pubilc finance service improvement software PSIS) አስለምቶ ወደ ትግበራ ለመግባት የተቋማት የእቅድ ክትትልና ድጋፍ ዳይሬክተር የበጀት ቡድን መሪ፣ ለግዥ ንብረት አስተዳደር እና ለፉይናስ ቡድን መሪዋች በሶፍትዊር አጠቃቀም ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ መስጠት ጀምሯል።

በግንዛቤ መስጫ መድረክ ላይ የፖላንና ኢኮኖሚ ልማት ኮሚሽን ኃላፊ አቶ ኃይለማሪያም ዳዲ እንደተናገሩት የመደበኛ እና የካፖታል በጀት የዝውውር ስርአትን ለማዘመን እና የተዛነፉ አሰራሮችን ለመደገፍ መመሪያውን በተከተለ አግባብ ተፈትሾ የአውቶሜሽን ሶፍትዌር ተዘጋጅቷል ብለዋል።

አቶ ኃይለማርያም አክለውም አቶሜሽን ተጠናቆ ሙሉ ለሙሉ ወደ ስራ መግባቱን እና የበጀት ዝውውር የአሰራር ስርአቱን በተከተለ አግባብ ያለው እንዲሆን ለማድረግ የተጀመሩ ስራዋች መኖራቸውን በመጥቀስ ተቋማት ከዚህ በፊት የበጀት ዝውውር ጥያቄ ለማቅረብ ከርቀት ቦታ በምጣ ሂደቱንም ለማስፈፀም ሁለት ሦስት ቀን ምልልስ ያደርጉ ነበር ከዚህ ባሻገም ተገቢውን መስፈርት ባልተሟላ መልኩ የዝውውር ጥያቄዋች እየቀረቡ እየተስተናገዱ ያሉበት ሁኔታ በመኖሩ በርካታ አላግባብ የሆኑ ዝውውሮች እየተከናወኑ ከመሆኑ አንፃር ይህን በአግባቡ ለመደገፍና የተዛነፉ አሰራሮችን ለመደገፍ መመሪያውን በተከተለ አግባብ ተፈትሾ አውቶሜሽኑ ተዘጋጅቷል ብለዋል።

ተቋማት ከአቅም በላይ በሆኑና ህጉ በሚፈቅዳቸው አግባብ ዝውውር ጥያቄ በሚያቀርቡበት ጊዜ ባሉበት ቦታ ሆነው ተገቢውን ጥያቄ በሲስተም የሚያቀርቡበት ሁኔታ ይፈጠራል መመሪያውን በተከተለ አግባብ ተፈትሾ ጥያቄያቸው ተቀባይነት እንዳገኘ እና እንዳላገኘ እንዲሁም ዝውውሩ ተጠናቆ ከተፈቀደ በኃላ ተቋሙ ላይ መምጣት ሳያስፈልግ በተቋማቸው ሆነው በሲስተም አውርደው የሚያገኙበት አሰራር ስርአት ተፈጥሯል ብለዋል።

ይህም በመሆኑ ከወረቀት ነፃ የሆነ ግንኙነት፣ ሂደቱን ለማስፈፀም የነበረን ምልልሶችን የሚቀንስ እና አሰራሩን የሚያዘምን፣ አላግባብ የሆኑ የመጠባበቂያ፣ የካፖታል፣ የመደበኛ በጀት ዝውውር ጥያቄ የሚያስቀር እና እቅዶች በታቀደላቸው አግባብ ብቻ እንዲከናወኑ የሚያደርግ እንዲሁም የእቅድና የክትትል ስርአቱ ውጤታማ ከመሆን አንፃር የራሱ የሆነ ፉይዳ ይኖረዋል ተብሎ ይገመታል ብለዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *