በተለያዩ የበጎ-አድራጎት ስራዎች ሁሉ ሁሌም ከወገኖቹ ጎን የሆነው የኤንዲ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ባለቤት እና ስራ አስኪያጅ የሆነው ኢንጂነር ነገራ ዱጉማ የረመዳን ፆም ወርን ምክንያት በማድረግ ለኪነ-ጥበብ ባለሞያዎች እና አርቲስቶች የምግብ ፍጆታ እንዲሁም የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ ችሏል ።
በዛሬው እለት 11 ለሚሆኑ የኪነ-ጥበብ ባለሞያዎች እና አርቲስቶች ድጋፍ የተደረገ ሲሆን የኤንዲ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ባለቤት እና ስራ አስኪያጅ የሆነው ኢንጂነር ነገራ ዱጉማ የረመዳን ፆም ወርን ምክንያት በማድረግ ድጋፍ ስላደረገላቸው በእጅጉ ደስተኛ መሆናቸውንም ነው የኪነ-ጥበብ ባለሞያዎች እና አርቲስቶች የተናገሩት ።


