ውይይቱ በዋናነት የፌዴራል ድጋፍ ሰጪ ልዑክ ቡድን በበጀት አመቱ በሁለት ዙር በዝግጅት ምዕራፍ እና በተግባር ምእራፎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተሰሩ የልማት ስራዎችን በሪፖርት እና በመስክ ጉብኝት የቀረቡትን ተመልክቶ ግብረ መልስ መስጠቱን ተከትሎ በተገኙት ግኝት ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑ ነው የተገለጸው።
በውይይቱም የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ ከድር ጁሀር በሀገር አቀፍ ደረጃ የተቀረጹ የልማት ፕሮግራሞችን ተግባራዊነትን ለማረጋገጥ የድጋፍ ሰጪ ልዑካን ቡድን ምልከታ እንደ አስተዳደር ህዝቡን ከልማቱ ተጠቃሚነቱን ከማረጋገጥ አንጻር የተከናወኑ ተግባራት አበረታች መሆናቸውን እና በተገኙት ግኝቶች ላይ እና በቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።
የድጋፍ ሰጪ ልዑካን ቡድኑ በአስተዳደሩ የተሰሩ የልማት ተግባራትን በጠንካራ ፣በውስንነት እንዲሁም በምርጥ ተሞክሮ በአስተዳደሩ የተገኙትን እንደ ሀገር ለማስፋት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ እንዲሁም በቀጣይ የትኩረት መስኮች ላይ አቅዶ በመስራት እና በቀጣይም በውጤት የሚለካ አፈጻጸም እውን ለማድረግ ታሳቢ ያደረገ የውይይት መድረክ መሆኑን የብልጽግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ክቡር ኢብራሂም ይሱፍ ገልፀዋል ።
የአስተዳደሩን ነዋሪ ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊ፣ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ተሳትፎውን ለማረጋገጥ በሰላም ግንባታ እና የበጎ አድራጎት ስራዎች ፣የእርሻ ና ግብርና ስራዎች ምርት እና ምርታማነትን ከማሳደግ አንጻር የተሰሩ ፣በአረንጓዴ አሻራ፣በሌማት ቱርፋት፣በኢንድስትሪ ልማት ፣ ገበታ ለትውልድ በከተማ ጽዳት እና ውበት የተሰሩ ፣ የስራ እድል ፈጠራ ፣የመንግስት ገቢን ከማሳደግ አንጻር ፣በትምህርት ለትውልድ ፣ በጤና እንዲሁም የአመራር እና የአባላት የአቅም ግንባታ ስልጠና የተመለከቱ የትኩረት መስኮች ትግበራ የመጡ ተጨባጭ ለውጦች የተመለከቱ መሆናቸውን ኃላፊው ተናግረዋል ።
በአስተዳደሩ በገጠር በተፋሰስ የተሰሩ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ፣ምርትና ምርታማነትን ከማሳደግ ፣በሰላም እሴት ግንባታ ድሬዳዋ ሰላሟ የተጠበቀ እንዲሆን በማስቻል አስተዳደሩን ተመራጭ በማድረግ በኩል የተሰሩ ስራዎች እንደሀገር ተሞክሮ ተወስዶ የማስፉት ስራዎችን ሊሰሩ እንደሚገባ እና በቀጣይም ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ ተገልጿል።


