ከድሬዳዋ የንግድና ኢንደስትሪ ማእከልነት ጎዞ ፍጥነት ጋር እኩል መራመድ የሚችል የሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ ልማት ስራ አስፈላጊ መሆኑ የተገለጸው ከአርባ ስድስት ሆቴሎች ለተውጣጡ አንድ መቶ ስልሳ ሰራተኞች ስልጠና ማጠናቀቂያ መድረክ ላይ ነው ፡፡
ለተከታታይ አራት ቀናት የድሬዳዋ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ከሆቴል ባለንብረቶች ማህበር ጋር በመተባበር የተሰጠውስልጠና የሆቴል ምግብና መጠጥ መስተንግዶና እንግዳ ተቀባይ ሰራተኞች አቅም በማጎልበት፤ የአስተዳደሩን የቱሪስት መዳረሻዎችና አማራጮች እንደዚሁም የኢንቨስትመንትና የንግድ አማራጮችን በቂ መረጃ የመስጠትና የማስተዋወቅ ስራን እንዲሰሩ ጭምር ያስችላል ብለዋል የድሬዳዋ አስተዳደር ንግድ ኢንደስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አብዲ ሙክታር ፡፡
ስልጠናው የአስተዳሩን በጎ ገጽታ ከመገንባት አኳያም ያለው ሚና የጎላ መሆኑን ጠቅሰው የድሬዳዋ የፍቅር ተምሳሌት ሰብእና ማሳያ መስተዋት ሆነው እንዲሰሩ መሰል የአቅም ግንባታ ስራዎች በተከታታይ መስራት እንዳለባቸው ኃላፊው ተናግረዋል ፡፡
ለስራ ለንድግና ለስብሰባ ብሎም ለሃይማኖታዊ ክብረ በዓላትና መሰል ጉዳዮች የሚመጡ ደንበኞቻቸው ስለ ድሬዳዋ የቱሪዝም መስህቦችና መዳረሻዎች ሲጠይቋቸው በቂ መረጃ ለመስጠት ያላቸው ግንዛቤ አናሳ በመሆኑ እንደሚቸገሩ ገልጸው በዚህ ረገድ ያለባቸውን ክፍተት ለመሙላት የሚያስችል ተከታታይ የአቅም ግንባታ ስልጣና እንደሚያስፈልጋቸው ተናግረዋል ፡፡
የድሬዳዋ አስተዳደር ንግድና ኢንዲስትሪ ቢሮ የባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት የቱሪዝም ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ነኢማ ኢብራሂም በበኩላቸው ድሬዳዋን ተመራጭ የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው ፤ የድሬዳን የቱሪዝም መዳረሻዎችና መስህቦች ከማተዋወቅ አንጻር ሰልጣኖቹ ያነሷቸውን የአቅም ክፍተት ለመሙላት ከሚሰሩ ስራዎች ውስጥ አንዱ አሁን ለሆቴል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የተሰጠው ስልጠና መሆኑን ጠቅሰው ሌሎች ቀጣይ ስራዎችም እንደሚከናወኑ ገልጸዋል፡፡
በተለይም ድሬዳዋን የቱሪዚም ኮንፍረስ መዳረሻ ከማድረግ አኳያ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን አስመልክቶ ለተነሳላቸው ጥያቄም ኃላፊዋ በርካታ እንግዶችን ተቀብለው የማስተናገድ አቅማቸው ከፍተኛ የሆኑ አዳዲስ ሆቴሎች እየተገነቡ መሆናቸውን ገልጸው ግንባታቸው ተጠናቅቆ ወደ ስራ ሲገቡ ድሬዳዋን የንግድና ኢንደስት ማእከል ለማድረግ ከሚሰራው ስራ ጎን ለጎን የኮንፍረንስ ቱሪዝምም አብሮ እንዲስፋፋ ትልቅ ድርሻ እንደሚኖራቸው ብለዋል ፡፡
የሆቴልና ቱሪዝም ዘርፉ የሚሰጠው አገልግሎት የደንበኞችን እርካታና ፍላጎት ያሟላና ዘመናዊ እንዲሆን ለማስቻል በዘርፉ የሚሰማሩ ሰራተኞች በትምህርና በስልጠና የበቁ እንዲሆን ለማስቻም በመስኩ የሰለጠኑ ባለሞያዎችን የሚያፈሩ ተቋማት መንግስትና በግል ባለሀብቶች ሊስፋፉ እንደሚገባም በስልጠናው ማጠቃላያ መድረክ ላይ ተገልጿል፡፡


