የቀደመ የጀግንነት ታሪኮቻችንን ድህነትን ድል በማድረግ መድገም እንደሚገባ ተገለፀ

ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለተሟላ ሃገራዊ ሉአላዊነትና ክብር በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ህዛባዊ ውይይት ተካሂዷል።

በመድረኩ የድሬደዋ አስተዳደር ከንቲባ የተከበሩ ከድር ጁሀር ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ የተቃጣባትን የውጭ ወረራና የገዥነት አስተሳሰብን በዜጎቿ አንድነት በመመከት ሉዓላዊነቷን ማስከበሯ ከሀገራችን አልፎ ለሌሎች አፍሪካ ሀገሮች የነፃነት ተምሳሌት ለመሆን በቅታለች፡፡ ይሁን እንጂ የሀገራችን ህዝቦች ለነፃነታቸው የተፋለሙትን ያክል በየጊዜው በሚፈጠሩ ጦርነቶችና እጅግ ኋላቀር የሆነ አስተሳሰብ ድህነትን የተላመዱ እስኪመስሉ ድረስ ለዘመናት አብረው መዝለቁን አስታውሰዋል፡፡

ስለሆነም የተረጅነትና ልመና መንፈስን በዘላቂነት በመለወጥ ሗላቀር አስተሳሰብና የሥራ ባህል በመስበር የበለፀገች ኢትዮጵያን በጋራ ለመገንባት በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ አማካይነት በተጀመረው ‘መፍጠር እና መፍጠን’ እሳቤ የብልጽግና ፓርቲ እና መንግሥት ይህን የሀገርን ሉዓላዊነት እና ክብር አደጋ ላይ የጣለ ጉዳይን ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ችግሩን ከመሠረቱ ለመፍታት በከፍተኛ ቁጭት እና እልህ የተቀናጀ እንቅስቃሴ መጀመሩን ገልፀዋል፡፡

በዛሬው ዕለትም በአስተዳደራችን የተካሄደው ህዝባዊ ውይይት ዋነኛ ዓላማ በሀገራችንም ሆነ በአስተዳደራችን ሥር ሰዶ የቆየውን የተረጂነትና ልመና አስተሳሰብ በማስወገድ ነዋሪውን ወደ ላቀ የምርታማነት ደረጃ ማሸጋገርና በቤተሰብ ደረጃ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና ሀገር በቀል የመረዳዳት ሥርዓት ለመገንባት የሚያስችል ምቹ ነባራዊ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ከነዋሪው ጋር መግባባት ላይ ለመድረስ እንደሆነ ከንቲባው ጠቁመዋል፡፡

በተመሳሳይ የብልፅግና ፓርቲ የድሬደዋ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊና በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት ተጠሪ አቶ ኢብራሂም ይሱፍ ኢትዮጵያ ቀደምት የስልጣኔና የጀግንነት ተምሳሌት ብትሆንም ድህነትን በማሸነፍና የቀደመ የጀግንነት ገድላችንን በድህነት ላይ መድገም አለምቻላችን የታሪክ እጥፋት መፈጠሩን ገልፀዋል።

ብልፅግና ፓርቲ ከጅምሩ የኢትዮጵያን ሉአላዊነት ክብር በልጆቿ የጋራ ጥረት እውን ለማድረግ በተለይም ወጣቱ ትውልድ ልመናን የሚጠየፍ ሰርቶ የመበልፀግ ዝንባሌው ያደገ እንዲሆንም ፓርቲው በፅኑ አቋም እንደሚሰራ አቶ ኢብራሂም አብራርተዋል።

በአገራችን ስር ሰዶ የቆየውን የተረጂነት አስተሳሰነብ በማስወገድ በቤተሰብ ደረጃ የምግብ ዋስትናን በማረጋጥ እርስ በእርስ የመረዳዳትን ባህል ለበማጎልበት የምክክር መድረኩ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።

በተጨማሪ የልማት መርሃ-ግብሮቻችን አፈፃፀም ለማሻሻል፣ የተረጂነት አስተሳሰብና ተግባርን ለመቀነስ፣ ተረጅ የህብረተሰብ ክፍሎችን በእርስ በርስ የመረዳዳት ባህል በዘላቂነት ከተረጅነት ተላቀው እራሳቸውን እንዲችሉ ለማድረግ እና የአካባቢያችንን ችግሮች በራስ አቅም ለመፍታት ሀገር በቀል ሥርዓት ዘርግቶ እንደሚሰራም አቶ ኢብራሂም ገልፀዋ።

በውይይቱ ጉዳዩን የተመለከተ ሰነድ ቀርቧል፡፡ በመቀጠልም በአስተዳደሩ የሚገኙ የተላያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በውይይቱ የታደሙ ሲሆን አገራዊና አስተዳደራዊ ጉዳዮች በስፋት ተነስተዋል።

የተረጅነትና የልመና ገመናችንን፣ መንስዔውና አደጋው፣ መገለጫዎችና መውጫ መንገዳችን፣ የተረጂ ዜጎች ነባራዊ ሁኔታ፣ ወቅታዊ የብልፅግና ፓርቲ እና የመንግሥት አቋም እንዲሁም ከአመራሩ እና ከህብረተሰቡ የሚጠበቁ ጉዳዮችን በተመለከተ ለተነሱ የተለያዩ ጥያቄዎች በቂ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።

በዳግማዊ ፍቃዱ

ፎቶ፦ሰላም አበበ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.diredawacommunication.org

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/DDGCAB

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCQNCC5tcc6Jd9zCKcmzQ-eA

ቴሌግራም፦ https://t.me/DDGCAB

ትዊተር፦ https://twitter.com/DawaOffice

በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *