የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር፥ አቶ ጥላሁን ከበደ በድሬዳዋ አስተዳደር ጉብኝት አካሄዱ

ርዕሰ መስተዳድሩ ድሬዳዋ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር ፣ በብልፅግና ፓርቲ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በድሬዳዋ ቆይታቸውም በከተማ ስራ አስኪያጅ ፣ በግብርና ቢሮ ፣ በንግድና ኢንዱስትሪ ፣ በወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን እንዲሁም በስራ እና ክህሎት ቢሮ የተከናወኑ ፕሮጀክቶችን የጉብኝታቸው አካል በማድረግ ተዘዋውረው ቃኝተዋል።

የሌማት ትሩፋት የብልፅግና ራዕያችንን ለማሳካት ጨዋታ ቀያሪ ነው ያልነውን ዛሬ በተግባር በድሬዳዋ መመልከት ችለናል ሲሉ የገለፁት ርዕሰ መስተዳድሩ፥ ሰው ተኮር በሆነው የብልፅግና ፓርቲ የኑሮ ውድነትን እና የመኖሪያ ቤት ችግርን ከመቅረፍ እንዲሁም የስራ እድል ፈጠራን ከማመቻቸት አንፃር በድሬዳዋ የታየው ተመክሮ አመርቂ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

አያይዘው ቀጣይ በሚኖረው ህዝባዊ መድረክ ሀብት ይዞ የተረጂነት እና የጠባቂነት መንፈስን ማስወገድ ያለመቻል እሳቤ ላይ ትኩረቱን የሚያደርግ እንደሆነ ጠቁመዋል።

የአለም አቀፉን እግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) ማረጋገጫ ያገኘውን የእግር ኳስ መጫወቻ ሜዳን ፣ በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘውን የድሬዳዋ ቄራዎች ድርጅት ፣ ሰብሰርፌስ ዳም ፕሮጀክት ፣ የመልካ ጀብዱ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ፣ ሃስ የህክምና ቁሳቁስ ማምረቻ ፋብሪካ ፣ የዶሮ እና የወተት እርባታ ኢንተርፕራይዞች ፣ የጎሮ ዘመናዊ የችግኝ ጣቢያን ጨምሮ የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅን መመልከት ችለዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ በአስተዳደሩ በሚኖራቸው ቆይታ ከከተማ እና ገጠር ወረዳዎች ከተውጣጡ ከተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ጋር በሚደረገው የውይይት መድረክ ላይ እንደሚሳተፉ ይጠበቃል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *