ድሬዳዋን ለማልማት ሁሉም በየተሰማራበት ዘርፍ የበኩሉን አስተዋፆ መወጣት እንደሚገባው ተገለፀ

የድሬዳዋ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ከአፍረን ቀሎ የአትሌቲክስ ክለብ እና ከድሬዳዋ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጋር በመተበባር “ድሬዳዋን በጋራ እናልማ” በሚል መሪ ቃል የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ እና የማህበረሰብ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በዛሬው ዕለት በድምቀት አካሄደ።

በመረሀ ግብሩ ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ድሬዳዋን ለማልማት እንደዚህ አይነት እስፖርታዊ ዝግጅቶች በመከናወናቸው መደሰታቸውን ገልፀው፤ ሁሉም በተሰማራት ዘርፍ ድሬዳዋን ለማልማት የበኩሉን አስተዋፆ ማበርከት እንደሚገባው ተናግረዋል።

ክቡር ከንቲባው አያይዘውም ለፕሮግራሙ አዘጋጆች ምስጋናቸውን በማቅረብ በስፖርታዊ ዝግጅቶች የከተማችንን ልማት መደገፍ የቻልነው ድሬዳዋ ሰላማዊ ከተማ በመሆኗ ይህንን ሰላም በቀጣይም አጠናክሮ ማስቀጠል ያስፈልጋል በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የድሬዳዋ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ካሊድ መሐመድ በበኩላቸው የዛሬው ፕሮግራም ዋነኛ አላማ የድሬዳዋን ልማት መደገፍና ድሬ እንድትለማ የድሬዳዋ አስተዳደር ወጣቶችና እስፖርት ኮምሽን የበኩላችንን አስተዋፆ ለማበርከት እንዲሁም ማህበረሰቡ እስፖርታዊ እንቅስቃሴን እንዲያዳብር መሆኑን ጠቅሰው፤ የፕሮግራሙ ተሳታፊዎችንም አመስግነዋል።

በዚህ ፕሮግራም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አትሌቶች አትሌት ሻለቃ አሊ አብዶሼ እና አትሌት ሀምሳ አለቃ ወርቅውሀ ጌታቸውን ጨምሮ ሌሎችም ታላላቅ አትሌቶች ተሳታፊ ሆነዋል።

በውድድሩ አሸናፊ ለሆኑ አትሌቶችም የሜዳልያና የሰርተፍኬት ሽልማት ተበርክቷል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *