ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለቀድሞ ፕሬዚዳንት ሣሕለ ወርቅ ዘውዴ ምስጋና አቀረቡ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢትዮጵያን በፕሬዚዳንትነት ላገለገሉት ሣሕለ ወርቅ ዘውዴ በኢትዮጵያ መንግሥት ስም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የለውጡ አንዱ ዓላማ ሥርዓትን ማጽናት ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የሥራ ኃላፊዎች በሕግ የተሰጣቸውን ኃላፊነት በተሰጣቸው ጊዜ ይወጣሉም ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት ሌሎች ደግሞ በተራቸው እነርሱን ተክተው ሀገራዊ ዓላማን በትውልድ ቅብብል ከግብ ያደርሳሉም ሲሉ ገልፀዋል።

የሀገር ግንባታ የሚሳካው በዚህ መንገድ እንደሆነ ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ላለፉት ስድስት ዓመታት ኢትዮጵያን በፕሬዚዳንትነት ላገለገሉት ለክብርት ሣሕለ ወርቅ ዘውዴ በኢትዮጵያ መንግሥት ስም ምስጋና አቅርበዋል።

ዛሬ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሆነው ኃላፊነት የተቀበሉት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ሀገርና ሕዝብን በላቀ ሁኔታ የሚያገለግሉበት የኃላፊነት ዘመን እንዲሆንላቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *