ሀገራችን ኢትዮጲያ በተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት ( ዩኔስኮ ) በዓለም ቅርሶች መዝገብ ውስጥ የተካተቱ በርካታ የማይንቀሳቀሱ ቅርሶች ያሏት ሲሆን አሁን ደግሞ ለሰው ልጅ አስፈላጊ የሆነ የማይዳሰስ ቅርስ ነው የተባለው የሱማሌ-ኢሳ ማህበረሰብ የቃል ልማዳዊ ሕግ ( ሔር ኢሴ ) በ 19 ነኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት የሳይንስና የባሕል ድርጅት ( ዩኔስኮ ) ጉባኤ በማይዳሰሱ የሰው ልጅ ቅርሶች ወካይ ዝርዝር ውስጥ በዓለም አቀፍ ማህደር ሊፃፍ ተችሏል ።
የሱማሌ-ኢሳ ማህበረሰብ የቃል ልማዳዊ ሕግ ( ሔር ኢሴ ) በተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት ( ዩኔስኮ ) በዓለም ቅርሶች መዝገብ ውስጥ የተመዘገበበትን ሰርተፍኬት ይዘው በነገው እለት ድሬዳዋ የሚገቡ የልኡካን ቡድኖችን የአቀባበል መርሀ-ግብር አስመልክቶ በዛሬው እለትም ለሚዲያ አካላት ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰቷል ።
የሱማሌ-ኢሳ ማህበረሰብ የቃል ልማዳዊ ሕግ ( ሔር ኢሴ ) በተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት ( ዩኔስኮ ) በዓለም ቅርሶች መዝገብ ውስጥ በመመዝገቡ ለሀገራችን ብሎም ለአፍሪካም ትልቅ ኩራት መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ኢንጂነር ጀማል ኢብራሂም ተናግረው በነገው እለትም ” ሔር ኢሴ ” በዓለም ቅርሶች መዝገብ ውስጥ የተመዘገበበትን ሰርተፍኬት ይዘው ድሬዳዋ ለሚገቡ ልኡካን ቡድንም ደማቅ አቀባበል እንደሚኖርም ነው ኢንጂነር ጀማል ያስታወቁት።
በተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት ( ዩኔስኮ ) በዓለም ቅርሶች መዝገብ ውስጥ የተመዘገበውን የሔር ኢሴን ለመመልከት በቀጣይ በርካታ ቱሪስቶች ወደ ድሬዳዋ ሊመጡ የሚችሉበት አጋጣሚዎች እንደሚኖሩ የድሬዳዋ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ፅህፈት ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ ሚካኤል እንዳለ ተናግረው ቅርሱን በማስተዋወቅ እና በመጠበቅ እንዲሁም ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ በማድረግ ሂደትም ቢሆን ሀላፊነታቸውን እንደሚወጡም ነው አቶ ሚካኤል እንዳለ ያስታወቁት ።
በአለማየሁ አበበ
ፎቶ :- በሰላም አበበ


