በድሬዳዋ አስተዳደር የወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ ላይ ትኩረት ተደርጎ በመሰራቱ በርካታ ወጣቶች የስራ ባለቤት መሆናቸው ተገለፀ::

በዛሬው እለት የኢፌድሪ ማዕድን ሚንስተር ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝ ከድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀርና ከመስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በጋራ በመሆን በድሬዳዋ ወረዳ ሁለትና ሶስት አስተዳደር በውበት ሳሎን ስራ፣ በእንጨት ስራ ውጤቶች እንዲሁም በህትመት ስራ ላይ የተሰማሩ ወጣቶችን የስራ እንቅስቃሴ ተመልክተዋል።

እንዲሁም ደግሞ በወረዳ 3 አስተዳደር በ2017 በጀት አመት በልማት፣ በሰላም እሴት ግንባታ፣ በመልካም አስተዳደር፣ በሌማት ቱሩፋት፣ በክረምት የበጎ ፍቃድ ስራ እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች የተከናወኑ ዋና ዋና ስራዎች ላይ ለእንግዶች ማብራሪያና ገለፃ ተሰቷል።

በአጠቃላይ በድሬዳዋ አስተዳደር የወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ ላይ ትኩረት ተሰቶበት እየተሰራበት በመሆኑ በርካታ ወጣቶች የስራ ባለቤት መሆናቸው ተገልፆ፤ ይህም በቀጣይ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተጠቁሟል።

በጉብኝቱ ወቅት ያነጋገርናቸው የስራ እድል የተፈጠረላቸው ወጣቶች በበኩላቸው በዚህ መልኩ የስራ ቦታቸው በመጎብኘቱ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀው፤ አስተዳደሩ ላበረከተላቸው ሁሉን አቀፍ ድጋፍ አመስግነዋል።

በኤደን ሳሙኤል

ፎቶ:-አገኘሁ ሸዋረጋ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *