በድሬዳዋ በአስተዳደር ደረጃ የሰላም የዉይይት መድረክ የእዉቅናና ምስጋና መርሀ ግብር ተካሂዷል ።
የተካሄደዉን የሰላም የዉይይት መድረክ የእዉቅናና ምስጋና መር ግብር በይፋ የከፈቱት የድ/ድ/አስ/ ፍትህ ፀጥታና ህግ ጉዳዮች ቢሮ ሀላፊ አቶ አብዱሰላም አህመድ መላ ህብረተሰቡን ዋንኛ ባለቤት በማድረግ ባለፉት ግዜያት በተሰሩ የሰላምና ፀጥታ ስራዎች ዛሬ ላይ ዘላቂ ሰላምን ማምጣት ተችሏል ነዉ ያሉት
በእዚህም ድሬዳዋ በአላት ሰላም በሌሎች ተመራጭና ምሳሌ ለመሆን ቾላለች ያሉት አቶ አብዱሰላም ለእዚህም ሁልግዜ ለሰላሙ ቅድሚያ በመስጠት መላዉ የአስተዳደሩ ነዋሪ ሲየደርግና እያደረገ ላለዉ ሁሉን አቀፍ ድጋፍና አጋርነት የላቀ ምስጋናቸዉን አቅርበዋል። በቀጣይም ይሄዉ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት በመግለፅ።
በመድረኩ ነባራዊ ሁናቴን መሠረት ያደረገና ዘላቂ ሰላምን ማረጋጥ በሚቻልባቸዉ ሁኔታዎች ላይ ያተከረ የመወያያ ፁሁፍ ቀርቦ ሰፊ ዉይይትና ምክክር የተካሄደም ሲሆን ያለዉን ሰላም ይበልጥ አስጠብቆ ለማስቀጠል የድርሻቸዉን እንደሚወጡም ተሳታፊዎቹ ተናግረዋል።
በእዚሁ መድረክ ማጠቃልያ ባለፉት ግዜያት ለዘላቂ ሰላም መረጋገጥ ከፍተኛ ሚናና ድርሻ ለነበራቸዉ የተለያዩ የሰላም ኮሚቴና አደረጃጀት አመራሮችና አጋዥ ተቋማት የእዉቅናና የምስጋና የምስክር ወረቀት ከእለቱ የክብር እንግዶች እጅ ተበርክቶላቸዋል።
በፍትህ ፀጥታና ህግ ጉዳዮች ቢሮ አዘጋጆነት በተካሄደዉ በእዚሁ የሰላም ኮንፍረስ የእዉቅናና ምስጋና መርሀ ግብር የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የተለያዩ የአስተዳደሩና የወረዳ አመራሮች የሁሉም የአስተዳደሩ ቀበሌ የሰላም አደረጃጀት አመራሮች፣አጋዠ ተቋማትና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል ስል የድሬዳዋ አስተዳደር በፍትህ ፀጥታና ህግ ጉዳዮች ቢሮ


