ድሬ ማይክሮ ፋይናስ የብድርና ቁጠባ ተቋም የአገልግሎት ተደራሽነቱን ለማስፋት ባንክ ተደራሽ የማያደርጋቸው የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ለማድረግ በድሬዳዋ አስተዳደር 02 ወረዳ ሀሎሌ መንደር 8ኛ ቅርንጫፉን ከፍቶ አስመርቋል ።

በቅርንጫፉ የመክፈቻ ስነስርዓት ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የአስተዳደሩ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ሙሉካ መሐመድ እንደገለፁት ተቋሙ ባንክ ተደራሽ የማያደርጋቸውን የህብረተሰብ ክፍሎችና ሴቶችን ተጠቃሚ በማድረግ ረገድ የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ የሚገኝ ተቋም መሆኑን ገልጸዋል ።

ኃላፊዋ አያይዘውም ተቋሙ በዘርፉ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ረገድ የጀመራቸውን ስራዎች አጠናክሮ መስራት እንዳለበት አብራርተዋል ።

የድሬ ማይክሮ ፋይናስ የብድርና ቁጠባ ተቋም ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተሾመ አበበ በበኩላቸው እንደገለፁት ተቋማቸው አነስተኛ ገቢ ያላቸው እና የስራ ፈጠራና ክህሎት ኖራቸው የፋይናንስ አቅርቦት ችግር የገጠማቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች ተደራሽ በማድረግ አገልግሎት እየሰጠ ያለ ተቋም መሆኑን ተናግረዋል ።

ዋና ሰራ አስፈፃሚው አክለውም ተቋሙ የብድና ቁጠባ አገልግሎትና ከባንክ አገልግሎት ባሻገር በሊዝ ፋይናንሲንግ አማካኝነት የሥራ መንቀሳቀሻ ያጠራቸውን ሥራ ፈጣሪ ነዋሪዎች አስፈላጊ ከፍተኛ ግብዓትን በማቅረብ ተጠቃሚ ማድረጉን አብራርተዋል። በቀጣይም በዘርፉ አጠናክሮ እንደሚሰሩ ገልጸዋል ።

በምርቃት ሰነ ሰርአቱ ላይም ከፍተኛ አመራሮች የባንክ ሀላፊዎች፣ የሀይማኖት አባቶች እንዲሁም የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል ።

የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ የብድርና ቁጠባ ተቋም ከ20 ዓመታት በፊት በ1 ሚሊየን አንድ መቶ ሺ ብር ያህል በሆነ ካፒታል የተቋቋመ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ከ1 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ወለድ ና ወለድ አልባ ሊዝ ፋይናንስ አገልግሎቶችን እየሰጠ ይገኛል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *