በምረቃ መርሀግብሩም የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሀር ተገኝተው ባደረጉት ንግግር በሶማሌ ክልል ሲቲ ዞን የተመረቁት የልማት ፕሮጀክቶች በተለይም ለድሬዳዋ አስተዳደር ግብአት በመሆን አብሮ በማደግ በመልማት የህትማማች እና ወንድማማችነትን ይበልጥ የሚያጠናክሩ መሆኑን ተናግረዋል።
የድሬዳዋ አስተዳደርም የሶማሌ ክልል ለሚያከናውናቸው የልማት ስራዎች ከጎን በመሆን በአስተዳደሩ ካሉት ከደረቅ ወደብ፣ ከኢንዱስትሪ ፓርክ ጋር በማስተሳሰር በጋራ ለመልማት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግም ከንቲባ ከድር ጁሀር አስታውቀዋል።
በፕሮጀክት የምረቃ መርሀ ግብሩም የአብዲ ፋራህ የዶሮ እርባታ በ1.5 ቢሊዮን ብር ወጪ የተገነባ ሲሆን በቀን ከ14 ሺ በላይ እንቁላል ማምረት የሚችል እና ለበርካታ ወጣቶች የስራ እድል የፈጠረ መሆኑ ተገልጿል።
ዋቢ ግሩፕ ማርብል እና ግራናይት ፋብሪካ በ2.2 ቢሊዮን ዶላር ፋብሪካው የተገነባ ሲሆን ለ300 ወጣቶች የስራ እድል የፈጠረ መሆኑ ና የመጀመሪያ ምዕራፍ ምርት ማምረት መጀመሩ ተገልጿል።
ፋብሪካው ከውጪ የሚገባውን ግራናይት በመተካትም ረገድ አይነተኛ ሚና ያለው መሆኑ ተነግሯል።
በምርቃ ስነ-ስርዓቱም የድሬዳዋ አስተዳደር ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች፣ የሶማሌ ክልል የካቢኔ አባላት ፣ የሲቲ ዞን አስተዳዳሪ፣ የኢትዮጵያ በጅቡቲ ቆንጽላ ጽ/ቤት ሀላፊ፣ ፣የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በሰላም ለማ
ምስል:- አገኘው ሸዋረጋ


