በእግር ኳስ ሜዳ የሚፈጠሩ ግጭቶችን ለመቆጣጠር የሚያስችል ውይይት ተካሄደ::

የእግር ኳስ ውድድር ለግጭት መንስኤ በመሆን የእርስ በእርሳ እና የመንደር የአካባቢ ግጭቶች ሲከሰቱ ይስተዋላሉ ይህን ችግር ስር ስዶ በቀጣዩ ትውልድም እንዳይደገም ወጣቱን የማወያየትና ከእግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር የመግባባ ሰነድ በመፈራረም ስራዎችን መስራት እንደሚገባም ተገልፃል፡፡

የኢስተርን ዴቨሎፕመንት ኢኒሺቲቭ (EDI)ከላይፍ ኤንድ ፒስ ኢኒስትቲዩት አለም አቀፍ ድርጅት (LPI)ጋር በመተባበር ላለፉት አመታት ዘላቂ ሰላምን ማረጋገጥ የሚያስችሉ በርካታ ስራዎችን ሲያከናውን መቆየይቱ ይታወሳል ድርጀቱ በዛሬው እለትም በመንደር እና አካባቢ ለይቶ በኳስ ውድድር ጨዋታ ላይ የሚነሱ ግጭቶችን መቆጣተር በሚያስችሉ ጉዳዩች ላይ ከዘጠኙም ወረዳዎች ከተወጣጡ ወጣቶች እና አሰልጣኞች ጋር ውይይት አካሄዷል ፡፡

በውይይቱ ላይ የተሳተፉ የፖሊስ አባላት እና አሰልጣኞች እንዲሁም ወጣቶች በሰጡት አስተያየት የድሬዳዋ እግር ካስ ፌደሬሽን በሚያዘጋጀው ጨዋታ ሊነሱ የሚችሉ ችግሮችን እንዴት መፍታት እንችላለን የሚለውን ግንዛቤ ያገኙበት መድረክ መሆኑን ገልፀው ለቀጣይ ጊዚያትም የኳስ ውድድሮችን እንዴት መምራት እንዳለባቸው ግብአት የምንወስድበት መድረክ ሆኖ አግኝተነዋል ብለዋል፡፡

የኢስተርን ዴቨሎፕመንት ኢኒሺቲቭ (EDI)የፕሮጀክት ኦፊሰር አቶ አብዱመሊክ መሀመድ በሰጡት አስተያየት ድርጅቱ በሰላም ዙሪያ የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀው ወጣቱ የሰላም ስራዎች ላይ የነቃ ተሳትፎ እንዲኖራቸው ከ9 ወረዳ ለተወጣጡ የግር ኳስ ደጋፌዎች፣ አሰልጣኞች፣ የእግር ኳስ ስፖርት አመራር በተጨማሪም የውድድር ስነ-ስርአት ተቆጣጣሪዎች ለሰላም ኮሚቴና ለሀይማኖት አባቶች የእግር ኳስ ሜዳ ግጭቶች መንስኤና መፍትሄዎቻቻ ምንድናቸው በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የግንዘቤ ማስጨበጫው ተሰቷል ብሏል፡፡

ፕሮጀክት ኦፊሰር አቶ አብዱመሊክ ከዚህም ጋር አያይዘው በእግር ኳስ ሜዳ ሰላምን ለማስቀጠል ሁሉንም የኳስ ቤተሰብ በእኩል ሊያስተዳድር የሚችል የመግባቢያ ሰነድ ከእግር ኳስ ፊደሬሽን ጋር በጋራ በመሆን ተፈራርሞ ወደ ስራ እንደሚገባም በሰጠው አስተያየት ጠቁማል፡፡

በስልጠናው የተሳተፍ ወጣቶችም በቀጣይ በሰላም ማስጠበቁ የድርሻቸውን አስተዋፅኦ እንደሚያደርጉ በመግለፅ ከእግር ኳስ ፊዴሬሽኑ እና ከሰላም ኮሚቴ ጋር በጉዳዩ ላይ እየመከረ ችግሮች በመፍታት የሚሰሩ ኮሚቴዎችን ከየወረዳው ተወካዮቻቸውን በመምረጥ ስልጠናው ተጠናቋል፡፡

በትዕግስት ቶሎሳ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *