#DGC ታህሳስ 23/2017
በድሬዳዋ አስተዳደር ከዘጠና በላይ ሞዴል ኢንተርፕራይዞች የሚሳተፉበት አውደ ርዕይ እና ባዛር በዛሬ እለት በይፋ ተከፍቷል።
የሞዴል ኢንተርፕይዞች ኤግዚቢሽንና ባዛርን የከፈቱት የድሬዳዋ አስተዳደር የስራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው ናቸው።
አቶ ሮቤል ቢሮው የንግድ አውደ ርዕይና ባዛሮችን በማዘጋጀት ኢንተርፕራይዞቹን ከደንበኞቻቸው ጋር የገበያ ትስስር እንዲፈጥሩ ከማስቻል ባለፈ የገበያ ዋጋን በማረጋጋት የድርሻቸውን እንደሚወጣ ተናግረዋል።
መጪው የበዓል ወቅት እንደመሆኑ መጠን የዕለት ፍጆታ ውጤቶች ዱቄት፣ ስኳር፣ ዘይት፣ ዶሮና፣ እንቁላል፣ በስፋትና በጥራት መቅረባቸውን አቶ ሮቤል ገልፀው፤ ህብረተሰቡ በውድ ዋጋ ሲገዛቸው የነበሩ የባህል አልባሳት በተመጣጣኝ ዋጋ ኤግዚቢሽንና ባዛሩ ላይ እንደሚያገኙ ተናግረዋል።
ለተከታታይ አምስት ቀናት የሚቆየው አውደ ርዕይ የገበያ ትስስር ከመፍጠር ባለፈ ለኢንተርፕራይዞች በቂ ምርትና አገልግሎታቸውን የሚያስተዋውቁበት እድል ይፈጥርላቸዋል።
በበድሉ ሀይሌ
ምስል፦ አገኘው ሸዋረጋ


