#DGC ታህሳስ 23/2017
የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኤች አይቪ ኤድስን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ይቻል ዘንድ የትምህርት ቤት ሚኒ-ሚዲያ ሚና ማጎልበቻ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በዛሬው እለት ተሰጥቷል።
በዚሁም የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መድረክ ላይም በመገኘት ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ብሩክ ፈለቀ ኤች አይቪ ኤድስን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ይቻል ዘንድ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ ቢሆኑም ነገር ግን አሁንም ቀጣይነት ያላቸው ስራዎች መሰራት እንደሚገባ ተናግረዋል።
የአስተዳደሩ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮም የሚሰሩ ስራዎችን በቅንጅት በመስራት የተሻለ ውጤቶችን ለማምጣት ይቻል ዘንድ የግንዛቤ ማስጨበጫው መድረኮች ወሳኝ መሆናቸውን ነው አቶ ብሩክ ፈለቀ ያስታወቁት ።
በአለማየሁ አበበ
ፎቶ :- በሰላም አበበ


