በዛሬው እለት የነበረው የጉብኝት መርሀ-ግብርም ከመጀመሩ አስቀድሞ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀር እና የካቢኔ አባላት ከስራ ተቋራጮችና ከኮሪደር ልማት አስተባባሪዎች ጋር ውይይት ያካሄዱ ሲሆን በውይይቱም ስለ ኮሪደር ልማት ስራው አጠቃላይ ማብራሪያ እንዲሁም ገለፃ ተደርጎላቸዋል ።
በዚህም መሰረት የመጀመሪያው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ዕቅድ በጥሩ አፈፃፃም እየተከናወነ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀር ተናግረው ልማቱ ጥራትና ውበቱን ጠብቆ ሥራው መጠናከር እንዳለበትና አስቸኳይ መፍትሄ ለሚሹ ጉዳዮችም ካቢኔው አፋጣኝ ውሳኔ እንደሚሰጥም ነው ክቡር አቶ ከድር ጁሀር በእለቱ የገለፁት ።
ከውይይቱ በኋላም በአስተዳደር ላይ እየተሰሩ ያሉትን የኮሪደር ልማት ስራዎች ያለበትን አሁናዊ ሁኔታም የካቢኔ አባላቱ ጎብኝተዋል ።
በአለማየሁ አበበ
ፎቶ :- በአገኘው ሸዋረጋ


