ኮሌጁ ይህን ያስታወቀው በምስራቅ ኢትዮጵያ የሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ተቋማትን ጋብዘው የልምድ ልውውጥና ጉብኝት በተደረገበት ጊዜ ነው ፡፡
የምስራቅ ኢትዮጵያ የልህቀት ማዕከል የመሆን ራዕይን ሰንቆ የተነሳው ኮሌጅ ብቻውን ተጉዞ የትም እንደማይደረስ በመረዳት በምስራቅ ኢትዮጵያ የሚገኙ የቴክኒክ ሙያ ተቋማት ያለበቸውን ክፍተት የለየና የቀጣይ አቅጣጫን የቀየሰ ምክክርና ጉብኝት ማድረጋቸውን ተገልጿል ፡፡
ከኢንደስትሪ ትስስር በተመለከተ ኮሌጆች የኢንደስትሪዎችን በር ማንኳኳጥ እንደሚጠበቅባቸው በጉብኝቱ ተመላክቷል።
የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የቲቬት ስትረቴጂውን ተከትሎ ጠንክሮ እየሰራ መሆኑን ተረድቻለሁ ያሉት የሀሮማያ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ዲን አቶኃይሌ ንጉሴ በቀጣይም ከድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ጋር በጋራ ለመስራት ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን ገልፀዋል ፡፡
የጨርጨር ፖሊ ቴክኒክ ዲን የሆኑት አቶ ከዲር አባዲር የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ በራሱ ኢነደስትሪ ነው ያሉ ሲሆን አዲሱን የቴክኒክና ኢንደስትሪ መርህ ማለትም ከፍላጎት መር ወደ አቅርቦት መር በማሳደግ ከኢነደስትሪዎች ጋር ያለውን ትስስር ማሳደጉን ተናግረዋል ፡፡
በከበደ ካሳ
ካሜራ ሙሉዓለም ደሴ


