በከሸፈው ጥቃት 19 ሰዎች መገደላቸውን የሀገሪቱ መንግስት አስታውቋል። ጥቃቱ የደረሰው የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ በዋና ከተማዋ ኒጃሜና ከመንግስት ባለስልጣናት ጋር ከተገናኙ ከጥቂት ሰአታት በኋላ ነው።
በጥቃቱ ቢያንስ 19 ሰዎች ተገድለዋል የተባለ ሲሆን የሀገሪቱ የፀጥታ ኃይሎች ታጣቂዎች በዋና ከተማዋ ኒጃሜና የሚገኘውን የፕሬዚዳንቱን ግቢ ለመውረር ያደረጉትን ሙከራ መከላከል መቻላቸው ተገልፆል።
ረቡዕ አመሻሽ ላይ በፕሬዚዳንቱ ጽህፈት ቤት ላይ በተፈፀመው ያልተሳካ ጥቃት ቢያንስ 18 የታጠቁ ኃይሎች መገደላቸውን መንግስት የገለጸ ሲሆን አንድ የጸጥታ ኃይል አባል በጠመንጃ ውጊያ መሞቱን አስታውቋል። የቻድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የመንግስት ቃል አቀባይ አብዴራማን ኩልማላህ እንዳሉት “ከታጣቂዎቹ 18 ሰዎች ሞተዋል 6 ደግሞ ቆስለዋል” ሲሉ የተደመጡ ሲሆን ከተጠቂዎቹ መካከል ደግሞ “አንድ ሰው ሲሞት ሶስት ቆስለዋል” ብለዋል።
ከተኩስ ልውውጡ ከሰዓታት በኋላ ኩልማላህ በወታደሮች ተከበው እና ቀበቷቸው ላይ ሽጉጥ ይዘው በቪዲዮ የታዩ ሲሆን፣ “ሁኔታው ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር ውሏል የማተራመስ ሙከራው አልተሳካም ብለዋል።” ጥቃቱ የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ወደ ቻድ ካደረጉት ይፋዊ ጉብኝት ጋር መገጣጠሙ አስገራሚ አድርጎታል።
ተኩስ ከመጀመሩ ከሰዓታት በፊት ዋንግ ዪ ከቻድ ፕሬዝዳንት ማሃማት ኢድሪስ ዴቢ እና ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ተገናኝተው ነበር። በጥቃቱ ወቅት ዴቢ በፕሬዚዳንት ኮምፕሌክስ ውስጥ ነበር ሲል ኩላማላህ ተናግሯል። እ.ኤ.አ. በ2021 ዓመፀኞች የረዥም ጊዜ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ኢድሪስ ዴቢን ከገደሉ በኋላ ልጃቸው ዴቢ ሥልጣኑን የ
ተቆጣጥረዋል። አዛውንቱ ዴቢ በ1990ዎቹ መጀመሪያ ላይ መፈንቅለ መንግሥት ካደረጉ በኋላ ቻድን ይገዙ ነበር።
አንድ የደህንነት ምንጭ ለፈረንሳይ የዜና ወኪል AFP እንደገለፀው ታጣጥዎቹ የቦኮ ሃራም ታጣቂ ቡድን አባላት ናቸው ያለ ቢሆንም ኩልማላህ ግን “ምናልባት ላይሆኑ ይችላሉ” በማለት በምትኩ የሰከሩ “ፒድስ ኒኬልስ” በማለት ገልጿቸዋል።
ምንጭ፡ Fana Tv


