በጎነት እና አብሮነት ለኢትዮጲያ ከፍታ በሚል መሪ ሀሳብ በድሬዳዋ አስተዳደር የ 2016 ዓ.ም የክረምት ወራት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት የእውቅናና የምስጋና መርሀ-ግብር በዛሬው እለት ተካሂዷል ።
በዚሁ መርሀ-ግብር ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀር በ 2016 ዓ.ም የክረምት ወራት የበጎ ፍቃድ እድሳትና ላይ 238 አዳዲስ ቤቶችን ከመገንባት ባለፈ 72 ቤቶች እድገትና ጥገና ስራ በማከናወን አቅመ ደካሞችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ተናግረው መንግስታዊና ህዝባዊ አካላት ፣ ባለሀብቶች ፣ በጎ-ፍቃደኛ ወጣቶች ፣ የወጣት አደረጃጀቶች ፣ የአስተዳደሩ የከተማ ወረዳ እንዲሁም የገጠር ወረዳዎች ፣ በየደረጃው ያሉ አመራሮች እና ባለሞያዎች ላደረጉት አስተዋፆም ክቡር አቶ ከድር ጁሀር በእለቱ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።
በ 2016 ዓ.ም የክረምት ወራት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት በ 14 የስምሪት መስኮች ከ 98 ሺህ በላይ የሚሆኑ በጎ ፍቃደኞችን ማሳተፍ መቻሉን የድሬዳዋ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ካሊድ መሀመድ ተናግረው በዚሁ የክረምት ወራት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ላይም ከ 296 ሺህ በላይ የሚሆኑ ነዋሪዎች ተጠቃሚ ከመሆናቸውም በላይ 120 ሚሊዮን ብር ማዳን መቻሉንም ነው አቶ ካሊድ መሀመድ የተናገሩት ።
በክረምት ወራት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ላይ አስተዋፆ ላበረከቱም ከእለቱ የክብር እንግዶች የእውቅና ሰርተፍኬት ተበርክቶላቸዋል ።
በአለማየሁ አበበ
ፎቶ :- በአገኘው ሸዋረጋ


