በዛሬው የከሰዓቱ ውሎ የከተማና ገጠር ወረዳዎች የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ መድረክ የተካሄደ ሲሆን በከተማና በገጠር ወረዳዎች ላይ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ለመድረኩ ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።
የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ ከድር ጁሃር ወረዳዎች የአካባቢያቸውን ፅዳት በማጠናከር፣ የህብረተሰቡን ቅሬታ የወረዳው ሀላፊ እራሳቸው ቢሮ ተገኝተው እንዲፈቱላቸው፣ የኮሪደር ልማቱ የሚደርስባቸው ወረዳዎች ላይ ህብረተሰቡን አስቀድመው እንዲያወያዩ የሌማት ቱሩፋት እና ዲጂታል መታወቂያ አሰጣጥ ላይ ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ አቅጣጫ ሰተዋል።
በግምገማው ላይ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ ከድር ጁሃርን ጨምሮ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
በበድሉ ሀይሌ
ፎቶ፦መታን ሸዋፈራው


