”የአፈር ሀብታችን ለብልፅግናችን” በሚል መሪ ሀሳብ የ 2017 ዓ.ም የተቀናጀ የበጋ ወራት የተፋሰስ ልማት ስራዎች ማስጀመሪያ መርሀ-ግብር በበአስተዳደሩ በአራቱም የገጠር ክላስተሮች መካሄድ ጀምሯል።
በድሬዳዋ አስተዳደር ከለውጡ ማግስት ከተመዘገቡ በርካታ የለውጡ ስኬቶችና የህዝቡን ተጠቃሚነት በላቀ ደረጃ ተጠቃሚ ካደረጉ ስራዎች መካከል የተቀናጀ የበጋ ወራት የተፋሰስ ልማት በቀዳሚነት እንደሚጠቀስ በቢዮ አዋሌ ክላስተር በኬሀሎ ገጠር ቀበሌ ማስጀመሪያ መረሀ ግብሩን ያስጀመሩት የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ተናግረው በዘንድሮው የተቀናጀ የበጋ ወራት የተፋሰስ ልማት ስራዎችን በውጤታማነት ለማከናወን እና ቀደም ሲል በተፋሰስ ልማት ያከናወናቸውን ስራዎች ዘላቂ ጠቀሜታ እንዲሰጡ መንከባከብ እንደሚገባም ተናግረዋል።
በዘንድሮ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራዎች በአጠቃላይ በ 5,550 ሄክታር መሬት ላይ የአፈርና ውሀ ጥበቃ ስራዎችን በማከናወን በ 3 ነጥብ 7 በመቶ የመሬት መራቆትን በመቀነስ በየአመቱ በጎርፍ ሊወሰዱ የሚችለውን 48,685 ቶን ለም አፈር ለመታደግ የታቀደ እንደታቀደና በ 4,556 ሄክታር የእርሻ መሬት ላይ ደግሞ የእርጥበት እቀባ ስራዎችን በመስራት 11,000 አባዎራዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ መታቀዱንም ነው የድሬዳዋ አስተዳደር የግብርና ውሀ ማእድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ ኑረዲን አብደላ የተናገሩት ።
በአለማየሁ አበበ
ፎቶ :- በቴዎድሮስ ልኡልሰገድ


