በዕለቱ የክብር እንግዳ የብልፀግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ድሬዳዋ ዝናብ አጠር ብሎም የጎርፍ አደጋ ተጋላጭ እንደመሆኗ የማያቋርጥ የአፈርና ውሃ ሃብት ጥበቃ ስራ ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ ምርትና ምርታማነትን ማሻሻል ላይ አይነተኛ ሚና ይኖረዋል ብለዋል፡፡
”የአፈር ሀብታችን ለብልፅግናችን” የሚል መሪ ሃሳብን ያነገበው የዘንድሮ የተፋሰስ ልማት ትግበራ ከዚህ ቀደም የተፈጥሮ ማገገም፣የከብት መኖ መጨመር፣ምንጮች መጎልበታቸው፣የግል እና የአካባቢ ንፅህና መጠበቅ እንዲሁም በትምህርታዊ ንቅናቄ በኩል ሰፊ ድሎች መመዝገባቸው ተነግሯል፡፡
በቀጣይ ቀናት ጋራ ላይ ከሚሰሩ ተግባራት በተጨማሪ የፍግ ማጓጓዝ፣ቀራ ነቀላ፣የውሃ ፍሳሽ ማስወገጃ ፅዳት እና የመንገድ ጥርጊያ ስራዎች የሚሰሩ ሲሆን ለአረንጓዴ አሻራ ችግኝ መትከያ ጉድጓድ ቁፋሮም በዚሁ ንቅናቄ የሚከናወን መሆኑ ተጠቅሷል፡፡


