ባለፉት አመታት በተሰሩ የበጋ ወራት ተፋሰስ ልማት ሥራዎች ምርትና ምርታማነት እንዲጨመር እና የከርስ ምደር ውሃ እንዲጎለብት ማስቻላቸው ተገለፀ፡፡

የ2017 ዓ.ም የበጋ ወራ የተፋሰስ ልማትና የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስራ በቀለዓድ ክላስተር በሙዲ አነኖ የገጠር ቀበሌ ተጀምሯል፡፡

በድሬዳዋ ከሚገኙ ዝናብ አጠር ክላስተሮች መሀል ቀለዓድ ይጠቀሳል፡፡ባለፉት 12 ዓመታት በበጋ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት በተሰራ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስራ ለውጥ ከተገኘባቸው አካባቢዎች መሀል አንዱ በሆነው በዚህ ክላስተር ሙዲ አነኖ የገጠር ቀበሌ የ2017 የበጋ ወራት የተቀናጀ የተፈጥሮ ሀብቶች ጥበቃ ህዝባዊ ሥራ በአፈር እና ውሃ ስራዎች ተጀምሯል፡፡

በክላስተሩ ተገኝተው ዘመቻውን ያስጀመሩት የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ፥ የንግድ ኢንደስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሃላፊ አቶ ሀርቢ ቡህ ባስተላለፉት መልዕክት እንዳሉት በአስተዳደሩ የዝናብ እጥረትና በረሀማነትን ለመከላከልና ብሎም በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ የሚከሰቱ ጎርፍና መሰል ተፈጥሯዊ አደጋዎችን ከመከላከል አንጻር የተፈጥሮ ሀብቶችን መንከባከብ የሞት የሽረት ጉዳይ በመሆኑ ባለፉት ዓመታት በህዝቡ የተሰሩት ሥራዎች ውጤቶቻቸው በተጨባጭ መታየቱን አስታውቀዋል።

አቶ ሀርቢ አክለውም በተለይም ዝናብ አጠርና ቆላማ በሆነው በቀለዓድ ክላስተር የቀደሙት ዓመታት ሥራዎች የከርሰ ምድር ውሀን እንዲጎለብት ማስቻላቸውን ገልጸው በዘንድሮው ዓመትም ይህንን ውጤት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ በትጋት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

Dire tv

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *