የድሬዳዋ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ከ5 መቶ ሺ ብር በላይ የሚያወጡ መፅሀፍትን እንዲሁም የአሜሪካ ኤንባሲ ከ 1 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ ወንበሮችን፣ መፅሀፍቶችን፣ ላፕቶፕና ዴክስቶፕ ኮንፒተሮችን በተጨማሪም የተለያዩ የቴክኖሎጂ ቁሳቁሶችን ለድሬዳዋ የህዝብ ቤተ-መፃህፍት እና ቤተመዛግብት አበርክተዋል።
በስጦታ የተበረከቱት መፅሀፍቶች በተለያዩ የትምህርት ደረጃ ላይ ለሚገኙ ተማሪዎች አጋዥ ሲሆኑ ለዩኒቨርቲ ተማሪዎች እና መምህራንም ለጥናትና ምርምር የሚያግዙ መሆናቸውም ተጠቁሟል።
በአጠቃላይም የተበረከቱት መፅሀፍትና የቴክኖሎጂ ቁሳቁሶች የማህበረሰቡን የንባብ ባህሉን የሚያዳብሩና በተለይም ወጣቶች ጊዜያቸውን በሱስና አልባሌ ቦታዎች ላይ ከሚያሳልፉ ይልቅ በንባብ እውቀታቸውን እንዲጨምሩ የሚያበረታቱና የቴክኖሎጂ ግንዛቤያቸውን እንዲያሳድጉ የሚረዳ መሆኑ ተመላክቷል።
በኤደን ሳሙኤል
ፎቶ:-ቴድሮስ ልዑልሰገድ


