የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሁለት የብድር ስምምነቶችን አፀደቀ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 1ኛ ልዩ ስብሰባ መንግስት ከዓለም አቀፉ የልማት ማህበር ጋር ያደረጋቸውን ሁለት የብድር ስምምነቶችን በአብላጫ ድምጽ አፅድቋል።

የብድር ስምምነቶቹ የፋይናንስ ዘርፉን ለማጠናከር እና የመንግስት አገልግሎትን ለማሻሻል የሚውሉ ናቸው ተብሏል።

የብድር ስምምነቶቹን አስመልክቶ የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ለምክር ቤቱ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፉ የልማት ማሕበር ጋር ያደረገችው የ700 ሚሊዮን ዶላር የብድር ስምምነት የፋይናንስ ዘርፉን ጤናማነትና ተወዳዳሪነት የበለጠ ለማሻሻል እንደሚያስችል ገልጸዋል።

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የካፒታል አቅምን እንደሚያሳድግ ገልፀው፤ ብድሩ የኢትዮጵያ ልማት ባንክን አሰራር ለማዘመን ያስችላልም ብለዋል።

ኢትዮጵያ ባለፉት አራት ዓመታት የዕዳ ጫናዋ እየቀነሰ መምጣቱንም ነው የተናገሩት።

ኢትዮጵያና ዓለም አቀፉ የልማት ማህበር ለዘመናዊ የመንግስት አገልግሎት ማሻሻያ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል የ70 ሚሊዮን ዶላር የብድር ስምምነትም ለምክር ቤቱ መነቅረቡን ኢዜአ ዘግቧል።

ምክር ቤቱ በብድር ስምምነቶቹ ላይ ከተወያየ በኃላ ስምምነቶቹን በአብላጫ ድምጽ አፅድቋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *