በብልፅግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ትላልቅ ውሳኔዎች ይወሰናሉ – አቶ አደም ፋራህ

የብልፅግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ የፓርቲው ቀጣይ አቅጣጫ የሚቀመጥበት እና ትላልቅ ውሳኔዎች የሚወሰንበት መሆኑን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማዕከል ኃላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ ገለፁ፡፡

የብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ከፊታችን ጥር 23 – 25 2017 ዓ.ም ድረስ ይካሄዳል፡፡

ጉባኤው “ከቃል እስከ ባህል” በሚል መሪ ቃል ነው በአዲስ አበባ የሚካሄደው።

ጉባኤውን አስመልክተው የፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳንት እና በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማዕከል ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

አቶ አደም ፋራህ በመግለጫቸው ጉባኤው የፓርቲው ቀጣይ አቅጣጫ የሚቀመጥበት እና ትላልቅ ውሳኔዎች የሚወሰንበት ነው ብለዋል።

ለጉባኤው የሚያስፈልጉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መጠናቀቃቸውን የገለፁት አቶ አደም ፋራህ፤ በጉባኤው ከሀገር ውስጥ ተሳታፊዎች በተጨማሪ 15 የውጭ ሀገር እህት ፓርቲ ተወካዮችም እንደሚታደሙ ገልፀዋል።

ጉባኤው ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ሁሉም ህብረተሰብ የተለመደውን ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪ ቀርቧል።

የብልጽግና ፓርቲ በዓለም በፓርቲ አባል ብዛት ከሚጠቀሱ ፓርቲዎች አንዱ ሲሆን አሁን ላይ ፓርቲው 15 ነጥብ 7 ሚሊዮን አባላት እንዳሉትም ተገልጿል።

EBC

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *