የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የበጀት፣ ኢኮኖሚ፣ ንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የድሬዳዋ አስተዳደር ንግድ፣ ኢንደስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮን የ2017 ዓ/ም የመጀመሪያ 6ወር እቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና የመስክ ምልከታ የመውጫ ውይይት አካሄደ

ቋሚ ኮሚቴው ባካሄደው የመስክ ምልከታ የመውጫ ዉይይት ላይ በክትትል እና ቁጥጥር ስራው በአካል ምልከታ ያደረገባቸው ተግባራት እና የ2017 በጀት ዓመት የ6ወር እቅድ አፈጻጸም የቢሮው አመራሮች በተገኙበት በመገምገም በጥንካሬ እና በውሰንነት የተነሱ ጉዳዮች ላይ በጋራ መግባባት ግብረ መልስ ተሰጥቷል ።

በዚህ የግምገማ መድረክ ላይ ከአሁን በፊት በቋሚ ኮሚቴው ለቢሮው የተሰጡ ግብረ_መልሶች አፈፃፀም፣ ህብረተሰቡ በውክልና አወጣጥ መድረኮች ያነሷቸውን ጥያቄዎች ፣ የቢሮው የመደበኛ እና የፕሮጀክቶች አፈፃፀም ሪፓርት ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጓል ።

በመድረኩ የድሬደዋ አስተዳደር የንግድ ኢንደስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ አብዲ ሙክታር በአነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ፣በኢንቨስትመንት ፣ በባህልና ተሪዝም ፣የንግድ ቁጥጥር እና የኑሮ ውድነት ፣የፕሮጀክቶች አፈፃፀም ጋር በተያያዘ ቋሚ ኮሚቴ አባላቶች ከቀረበው ሪፓርት እና በመስክ የተመለከቱት ጉዳዮች መነሻ በማድረግ ያነሷቸው ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ላይ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ተሰጥቷል ።

በመጨረሻም ቢሮው በ2017 ዓ/ም የመጀመሪያ 6 ወር እቅድ አፈፃፀም በሁሉም የስራ ዘርፎች አበረታች ተግባራት መከናወናቸውንና በውስንነት የተገመገሙ ትን በሁለተኛው 6 ወር እቅድ ውሰጥ ተካተው ሊሰራባቸው እንደሚገባ የበጀት፣ ኢኮኖሚ፣ንግድና ኢንደስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የሆኑት የተከበሩ ወ/ሮ አይናለም ተዘራ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

ለተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የቆየውን የመስክ ምልከታ አጠናቀዋል ።

በኤደን ሳሙኤል

ፎቶ:-ሙሉዓለም ደሴ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *