በ2017 በጀት አመት በመጀመሪያው 6 ወራት ብቻ በምግብ መድኃኒት ጤና እና ጤና ነክ ዘርፎች ላይ በተለይ በምግብ ተቋማት ህገወጥ ምግብ ቁጥጥር በ442 ተቋማት ላይ ቁጥጥር መደረጉን የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ የምግብ መድኃኒትና ጤና ነክ ቁጥጥር ዳሬክቶሬት ዳሬክተር ሲስተር ሰሬዶ ኡመር ተናግረዋል። በተደረገው ቁጥጥር 31 ተቋማት የታሸጉ ሲሆን 52 በሚሆኑ የምግብ ተቋማት ላይ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ መሰጠቱን ሲስተር ሰሬዶ ጠቁመዋል።
በድሬዳዋ አስተዳደር በተለያዩ የገበያ ማዕከል በችርቻሮ እና በጅምላ አከፋፋይ ንግድ ላይ በተሰማሩ ነጋዴዎች ላይ በተደረገው ቁጥጥር ግምታቸው ከ700ሺህ በላይ የሆኑ ደህንነታቸው ያልጠበቁ እና ጊዚያቸው ያለፈባቸው የምግብ ምርቶችን ማስወገድ መቻሉን ዳሬክቶሬት ዳሬክተሯ ተናግሯል።
የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ የምግብ መድኃኒትና ጤና ነክ ቁጥጥር ዳሬክቶሬት በመድኃኒት ችርቻሮና በጤና ተቋማት ቁጥጥር እንዲሁም ህገወጥ መድኃኒት ምርቶች ቁጥጥር ላይ ከ1ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ መድኃኒቶች ማስወገድ ተችሏል።
እንደ ሲስተር ሰሬዶ ኡመር አገላለጽ በአስተዳደሩ የኢትዮጵያ ደረጃን አሟልተው የሚሰሩ የጤና ተቋማት ሽፋን ለማሳደግ በ100 ጤና ተቋማት ላይ ቁጥጥር መደረጉን ተናግረዋል።
በትንባሆ ቁጥጥር ዘርፍ በ570ተቋማት ላይ ጥብቅ ቁጥጥር በማድረግ ከትንባሆ ነፃ የሆኑ ተቋማትን 72%ማድስ መቻሉን ጠቁመዋል።
የድሬዳዋ ማህበረሰብ በመንገድ ዳር የምግብ ንግድ ዘርፍ ላይ አብዛኛው የተሰማሩ እና ማህበረሰቡም የመንገድ ዳር ምግብ ተጠቃሚ በመሆኑ ተላላፊ እና ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች እንዳይጠቁ በንፅህና አጠባበቅ እና በምግብ ድህነት ማስጠበቅ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ ከመሰራቱ ባሻገር ተጠያቂነትን ለማስፈን ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ እየተሰራ መሆኑ ተጠቁሟል።


