ቀዳዴ ፋሚሊ ጠቅላላ ሆስፒታል ለማህበረሰቡ ነፃ የቅድመ የጤና ምርመራ አግልግሎት ሰጠ

በሀገራችን ከፍተኛ የጤና ተገዳሮት እየሆኑ የመጡትን የማይተላለፉ በሽታዎችን በመክላከል ረገድ የቅድመ የጤና ምርመራ አገልግሎት ትልቅ አስተዋጾ እንዳለው ተገለፀ፡፡

በታዳጊ ሀገራት ህዝብ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሱና አሳሳቢ ደረጃ ላይ ከደረሱ በሽታዎች ውስጥ ስኳር፣ ደም ግፊት እና የልብ ድካምና የመሳሰሉ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ይጠቀሳሉ፡፡ ቀዳዴ ፋሚሊ ጠቅላላ ሆስፒታል ነፃ የጤና ምርመራ አገልግሎት በከንቲባ ጽ/ቤት አስተዳደር ውስጥ ለሚገኙ ሰራተኞች እና ለአገልግሎት ለመጡ የማህበረሰብ ክፍሎች ሰጥቷል።

የቀዳዴ ፋሚሊ ጠቅላላ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ፈይሰል አህመድ እንደገለጹት ነፃ የጤና ምርመራ አግልግሎት ለማህበረሰቡ መስጠት ያስፈለገው በዋናነት ታካሚዎች ወደህክምና ተቋማት ሲመጡ የጤናቸውን ሁኔታ አስቀድሞ በማወቅ ህክምና እንዲያገኙ እንዲሁም ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ለማስቻል እንደሆነ ና አገልግሎቱን በአስተዳደሩ ህዝብ በብዛት በሚገኝባቸው አካባቢዎች የነጻ ቅድመ ምርመራ አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

መሰል በጎ ተግባራትም ላይ ሆስፒታሉ ተሳትፎውን እንደሚያጠናክር የገለጹት ሀላፊው ሆስፒታሉ ዘመን ያፈራቸው የህክምና መሳሪያዎችን ከውጪ በማስገባት ወደ ውጪ የሚደረጉትን ህክምና በማስቀረት እና በዚሁ ህክምና መሰጠት የሚያስችሉ አገልግሎቶቹንም መጀመሩን ተናግረዋል፡፡

የአገልግሎቱ ተጠቃሚ የሆኑ አካላትም ሲገልጹ የተደረገልን የጤና ምርመራ ወቅታዊ የጤና ሁኔታችንን ለማወቅ አስችሎናል ያሉ ሲሆን ይህ አይነቱ በጎ ተግባር ሊበረታታ ይገባል ብለዋል፡፡

በሰላም ለማ

ምስል፡- ሰላም አበበ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *