“የኢትዮጵያን የማንሰራራት ጉዞ ለማሳካት ቃላችንን በድጋሚ አድሰናል” – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

የኢትዮጵያን የማንሰራራት ጉዞ እና የህዝባችንን መሻት ለማሳካት ቃላችንን በድጋሚ አድሰናል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለፁ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው፤ ብልፅግና ፓርቲ የጠራ ሀሳቡንና ትክክለኛ ፖሊሲዎቹን በትጉህ አመራርና አባላቱ በመፈጸም በአስደማሚ ድሎች ጉዞውን ቀጥሏል ብለዋል።

ፓርቲያችን ከእነዚህ ድሎች ማግስት ባካሄደው ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ሀገርና ህዝብን እንድናገለግል አደራ ተሰጥቶናል ሲሉም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያን የልዕልና ጉዞ እናሳካዋለን ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የኢትዮጵያን የማንሰራራት ጉዞ እና የህዝባችንን መሻት ለማሳካት ቃላችንን በድጋሚ አድሰናል ብለዋል።

ሁለንተናዊ ክብርና ብልፅግናን የተቀዳጀች ኢትዮጵያን ለትውልዱ ለማስረከብ ለፈተናዎች ሸብረክ ሳንል ያለ እረፍት እንደምንሠራ ለመላው ህዝባችን ማረጋገጥ እፈልጋለሁ ሲሉም አክለዋል።

EBC

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *