በጉብኝቱም የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ተወካይ እና የአስተዳደሩ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሙሉካ መሀመድ የጉብኝቱ ዋነኛ አላማ ከዕቅድ አንፃር የስራዎች ሂደት ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ለመመልከት፤ እንዲሁም በስራ ሂደት የገጠሙ ችግሮች ካሉም በሳይት በመገኘት ከኮንትራክተሮችና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ተወያይቶ ችግሮችን ለመፍታት መሆኑን ተናግረዋል።
ወ/ሮ ሙሉካ አያይዘውም በድሬዳዋ አስተዳደር እየተከናወነ የሚገኘውን የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት በሁሉም ሳይት በጥሩ ሁኔታ እየተከናወነ እንደሚገኝና፤ ስራውን በተቀመጠለት ጊዜና ጥራት ለማጠናቀቅ ስራዎችን በርብርብ እየተሰሩ እንደሆነ አመላክተዋል።
በጉብኝቱ የድሬዳዋ አስተዳደር ካቢኔዎች እንዲሁም በአስተዳደሩ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች የኮሪደር ልማቱን አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ ተመልክተዋል።
በኤደን ሳሙኤል
ፎቶ:-ቴድሮስ ልዑልሰገድ


