የብልፅግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ በሁለተኛ ቀን ውሎው በልዩ ልዩ አጀንዳዎች ላይ እየተወያየ ይገኛል።
በትናንትናው እለት በደማቅ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት የተጀመረው የፓርቲው ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ በጠዋቱ ክፍለ ጊዜው በጉባኤው አዘጋጅ አብይ ኮሚቴ ሪፖርት እና በሁለተኛው ጉባኤ የስብሰባ ሥነ-ሥርዓት ደንብ ላይ ተወያይቶ አጽድቋል።
በተጨማሪም ጉባኤው በማዕከላዊ ኮሚቴው በቀረበ ሪፖርት ላይ ጥልቅ ውይይት ያደረገ ሲሆን ሪፖርቱን በውይይት አዳብሮ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።
በቀጣይ መርሀ ግብሩም በቀሪ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎች ያሳልፋል፣ ቀጣይ አቅጣጫዎችንም ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል።
EBC


