በድሬዳዋ የአሰልጣኞች የካፍ ዲ(D) ላይሰንሲንግ ስልጠና ተጀመረ::

የወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ከእግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር ያዘጋጁት የአሰልጣኞች የካፍ ዲ(D) ላይሰንስ ስልጠና በዛሬው ዕለት በራስ ሆቴል ለሰልጣኞች ስልጠና በመስጠት ተጀምሯል

ስልጠናውን በይፋ መጀመሩን ያበሰሩት የድሬዳዋ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት የሆኑት ኮምሽነር አለሙ መግራ ይህ ስልጠና እንደ ድሬዳዋ እግርኳስ እድገት እንደ ጅምር መወሰድ አለበት እንድሁም ድሬዳዋ የእግር ኳስ ከተማ መሆኗን በመጠቆም ሰልጣኞች ከተወዳዳሪነት ውጭ ሙያዊ ብቃት ማገኘት እንዳለባቸውም ጠቁመዋ።

በመጨረሻም በስልጠናው ዘርፍም የድሬዳዋ የእግር ኳስ ታሪክን መድገም አለብን ብለዋል።

የወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑት ካሊድ መሃመድ በበኩላቸው አሰልጣኞች የስልጠናውን እድል መጠቀም እንዳለባቸው ተናግረዋል።

በራስ ሆቴል በነበረው የስልጠናው የመክፈቻ ስነስርዓት ላይ ስልጠናው ለሚቀጥሉት 11 ቀናት እንደሚሰጥ ተጠቁሟል።

ስልጠና በዘንድሮው ዓመት ለሁለተኛ ጊዜ እየተከናወነ ሲሆን ከሁለት ዓመት በፊት መሰጠቱን እናስታውሳለን በቀጣይም ስልጠናው ተጠናክሮ በመቀጠል የካፍ ሲ እና ቢ ላይሰንስ ስልጠና እንደሚሰጥ ተገልፃል።

ለአስራ አንድ ቀን የሚቆየው ስልጠና ባዛሬው ዕለት በይፋ ኢንስትራክተር መሰረት ማኔ አማካኝነት ተጀምሯል በዚህ ስልጠና ላይ አንድ ሴት እንዲሁም 29 ወንዶች በድምሩ 30 ሰልጣኞች እየተሳተፍ ይገኛሉ

Diretv

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *