በሁለተኛው የብልፅግና ፓርቲ መደበኛ ጉባዔ የተቀመጡ አቅጣጫዎችን በውጤታማነት በመፈፀም የሀገሪቱን ሁለንተናዊ ብልፅግና ማፋጠን እንደሚገባ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ ገልጸዋል፡፡
ምክትል ፕሬዝዳንቱ ጉባኤው በስኬት እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ጉባኤው በአንደኛው የፓርቲው መደበኛ ጉባዔ የተቀመጡ አቅጣጫዎች አፈፃፀም በጥልቀት የተገመገሙበት፣ የፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ የተሻሻለበት እንዲሁም ነፃ፣ ፍትሐዊ እና ዴሞክራሲያዊ የአመራር አባላት ምርጫ የተካሄደበት መሆኑን አስታውሰዋል፡፡
በጉባኤው ፓርቲው እስካሁን ያስመዘገባቸው ስኬቶች እና ድሎች ወደ ላቀ ደረጃ የሚደርሱበት አቅጣጫዎች መቀመጣቸውንም አስታውቀዋል፡፡
በመሆኑም ”በጉባዔው የተቀመጡትን አቅጣጫዎች በውጤታማነት በመፈፀም የሀገራችንን ሁለንተናዊ ብልፅግና የማረጋገጥ ጉዞ እንድናፋጥን ሁላችንም በቁርጠኝነት እንድንሰራ ጥሪዬን አቀርባለሁ” ማለታቸውን ከማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡ ፡


